ስራህ ፡ ግሩም (Serah Gerum) - ህሊና ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ህሊና ፡ ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

፪
(2)

አልበም
(Egziyabeher Tilik)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:47
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

ስራህ ግሩም (Track 12)

(ግሩም፣ ግሩም፣ ግሩም እና ድንቅ….. ነህ እግዚአብሔር )

አሻግርሻለሁ ስትል የታመንከው
በራስህ ጉልበት በራስህ ጉልበት
እኔ አቆምሻለሁ ስትል የታመንከው
በራስህ ጉልበት በራስህ ጉልበት
ጥያቄ የለኝም ጥርጥር አይገባኝ
ስራው የእኔ እኮ ነው ብለኸኛል ታማኝ (2x)

ኦሆ እግዚአብሔር ድንቅ ነህ
ኦሆ ክንድህን አይቻለሁ
ኦሆ የደነደነውን ልብ
ኦሆ እንደሰም ስታቀልጠው
ኦሆ ነፍሴ ተማርካለች ኦሆ እስከለዘላለም
ኦሆ ከሀሳብህ ውጪ ኦሆ የሚወስደኝ የለም

ስራህ ግሩም እና ድንቅ ነው (3x)
እኔ እላለሁ
ክብርህ ግሩም እና ድንቅ ነው (3x)
እኔ እላለሁ

አቤት በሰራኸው ባደረከው ሁሉ
እጅግ ተደንቄ ተገርሚያለሁ
ክብርህን ስትገልጥ ዝናህን ስታሳይ
አጋዥ አትፈልግም አንት የሌለህ ከልካይ
ባደረከው ሁሉ በሰራህልኝ
ከተመስገን ሌላ የምለው የለኝ
ነገር ግን በፊትህ በክብርህ ውስጥ ሆኜ
ጌታ እልሀለሁ...

ስራህ ግሩም እና ድንቅ ነው (3x)
እኔ እላለሁ
ክብርህ ግሩም እና ድንቅ ነው (3x)
እኔ እላለሁ

ኦሆ ሰማያት ክብርህን ኦሆ ክብርህን ያወራሉ
ኦሆ ፍጥረታትም ደግሞ ኦሆ ይመሰክራሉ
ኦሆ እነርሱ ገብቷቸው ኦሆ ይገባዋል ካሉ
ኦሆ እኔ እኔማ እንዴት አልል ኦሆ ስራህ ግሩም

ስራህ ግሩም እና ድንቅ ነው (3x)
እኔ እላለሁ
ክብርህ ግሩም እና ድንቅ ነው (3x)
እኔ እላለሁ