በረከቴ (Berekete) - ህሊና ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ህሊና ፡ ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

፫
(3)

አልበም
(linurilih)

ቁጥር (Track):

፲ (10)

ርዝመት (Len.): 7:43
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

"" has no sub pages.

በረከቴ

እኔ ፡ የምሻው ፡ በረከት (ኦ)
የውስጥ ፡ የልቤ ፡ ጥማት (አ)
የሁሉ ፡ ነገሬ ፡ መልስ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ መገኘትህ
የእግዚአብሄር ፡ ልጅ ፡ መገኘትህ
በቤቴ ፡ ውስጥ ፡ መገኘትህ
በመውጣቴ ፡ አብሮነትህ
በመግባቴ ፡ አብሮነትህ
እኔ ፡ የምሻው ፡ በረከት (ኦ)
የውስጥ ፡ የልቤ ፡ ጥማት (አዋ)
የሁሉ ፡ ነገሬ ፡ መልስ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ መገኘትህ
የእግዚአብሄር ፡ ልጅ ፡ መገኘትህ
በጎዳዬ ፡ መገኘትህ
በመውጣቴ ፡ አብሮነትህ
በመግባቴ ፡ አብሮነትህ

በእውነቱ ፡ አንተ ፡ አይደለህ ፡ የበረከት ፡ ትርጉሙ
በእውነት ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ የበረከት ፡ መሰረት
በእውነቱ ፡ አንተ ፡ አይደለህ ፡ የበረከት ፡ ትርጉሙ
በእውነት ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ የበረከት ፡ መሰረት
የሰው ፡ ልጆች ፡ ሁሉ ፡ ስኬት
ከሀሳብህ ፡ ጋር ፡ መስማማት
የሰው ፡ ልጆች ፡ ሁሉ ፡ ስኬት
በፈቃድህ ፡ ስር ፡ መገዛት
የሰው ፡ ልጆች ፡ ሁሉ ፡ ስኬት
አንዱን ፡ ልጅህን ፡ በእውነት ፡ ማመን
የሰው ፡ ልጆች ፡ ሁሉ ፡ ስኬት
ከሀሳብህ ፡ ስር ፡ መገዛት

በረከቴ ፡ በረከቴ ፡ በረከቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እርስቴ
ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ድርሻዬ
በረከቴ ፡ በረከቴ ፡ በረከቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እንቁዬ
መድሀኒቴ ፡ መድሀኒቴ ፡ መድሀኒቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እርካታዬ

እንደ ፡ ሌዋውያን ፡ እንደ ፡ ካህናቱ
የእለት ፡ ክፍያዬ ፡ ድርሻና ፡ ደዋዜ
አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
ድንኳን ፡ ውስጥ ፡ አድራለሁ ፡ ይቅርብኝ ፡ ማረፍያ
ነፍሴ ፡ አትኩራለች ፡ በጉጉት ፡ ጥበቃ
ያንተን ፡ ውብ ፡ ከተማ
እንደ ፡ ሌዋውያን ፡ እንደ ፡ ካህናቱ
የእለት ፡ ክፍያዬ ፡ ድርሻና ፡ ደዋዜ
አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
ድንኳን ፡ ውስጥ ፡ አድራለሁ ፡ ይቅርብኝ ፡ ማረፍያ
ነፍሴ ፡ አትኩራለች ፡ በጉጉት ፡ ጥበቃ
ያንተን ፡ ውብ ፡ ከተማ
እጅህ ፡ የሰራትን ፡ መሰረትዋ ፡ የፀና
ዙፋንህ ፡ ያለበት ፡ የህይወት ፡ ወንዝ ፡ ውሀ
ሁሉም ፡ የሚረካበት ፡ ባንተ ፡ ህልውና
ያኔ ፡ ነው ፡ ሽልማት ፡ አክሊሌን ፡ ስደፋ
እጅህ ፡ የሰራትን ፡ መሰረትዋ ፡ የፀና
ዙፋንህ ፡ ያለበት ፡ የህይወት ፡ ወንዝ ፡ ውሀ
ሁሉም ፡ የሚረካበት ፡ ባንተ ፡ ህልውና
ያኔ ፡ ነው ፡ ሽልማት ፡ አክሊሌን ፡ ስደፋ

በረከቴ ፡ በረከቴ ፡ በረከቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እርስቴ
ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ድርሻዬ
በረከቴ ፡ በረከቴ ፡ በረከቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እንቁዬ
መድሀኒቴ ፡ መድሀኒቴ ፡ መድሀኒቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እርካታዬ

ምናየው ፡ ሁሉ ፡ እንደ ፡ ጢስ ፡ ያልፋል
ሰማይና ፡ ምድር ፡ ይጠቀለላል
ትንብት ፡ ይሻራል ፡ ህልምም ፡ ይሻራል
ህያው ፡ ቃሉ ፡ ግን ፡ ዘላለም ፡ ይኖራል
ምናየው ፡ ሁሉ ፡ እንደ ፡ ጢስ ፡ ያልፋል
ሰማይና ፡ ምድር ፡ ይጠቀለላል
ትንብት ፡ ይሻራል ፡ ህልምም ፡ ይሻራል
ህያው ፡ ቃሉ ፡ ግን ፡ ዘላለም ፡ ይኖራል

ህያው ፡ ቃሉ ፡ ህያው ፡ ቃሉ ፡ ህያው ፡ ቃሉ
ኢየሱስ ፡ እራሱ ፡ ነው
ህያው ፡ ቃሉ ፡ ህያው ፡ ቃሉ ፡ ህያዉ ፡ ቃሉ
ኢየሱስ ፡ እራሱ
በረከቱ ፡ በረከቱ ፡ በረከቱ
ኢየሱስ ፡ እራሱ ፡ ነው
በረከቱ ፡ በረከቱ ፡ በረከቱ
ኢየሱስ ፡ እራሱ