From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
|
|
ህሊና ፡ ካሳሁን (Hillina Kassahun)
|
|
|
|
፫ (3)
|
Silemwedih (Silemwedih)
|
| ቁጥር (Track):
|
፭ (5)
|
| ርዝመት (Len.):
|
7:14
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
|
የህሊና ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች (Albums by Hillina Kassahun)
|
|
"" has no sub pages.
|
ቆይቼ ፡ ልጥና ፡ ደጅህን
ደጋግሜ ፡ ላንኳኳ ፡ በርህን
የመንፈስህ ፡ ነኝ ፡ እረሃብተኛ
ሰርተኸኝ ፡ በሌላ ፡ እንዳልረካ
ይሄን ፡ አውቄ ፡ ነፍሴ ፡ ተሸኝፋ
እጅ ፡ ሰታለች ፡ እስከዘላለሟ
ብትወድ ፡ በሃይለኛው ፡ ንፋስህ
ብትወድ ፡ በነበልባል ፡ እሳት
ብትወድ ፡ ዝም ፡ ባለው ፡ ፀጥታ
ብትወድ ፡ በትንሿ ፡ ኮሽታ
ብቻ ፡ አንተ ፡ ና ፡ ብቻ ፡ አንተ ፡ ና
አንተ ፡ ብቻ ፡ ና ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ና
አስቀድሜ ፡ ፅድቅህን ፡ አስቀድሜ ፡ ፊትህን
አስቀድሜ ፡ ወደጏዳ ፡ አስቀድሜ ፡ በሬን ፡ ልዝጋ
መጀመሪያ ፡ ፅድቅህን ፡ መጀመሪያ ፡ ፊትህን
መጀመሪያ ፡ ወደጏዳ ፡ መጀመሪያ ፡ ላወጋህ
ፍለጋ ፡ ፍለጋ ፡ ፍለጋ
ቀኖቼ ፡ ይለቁ ፡ አንተን ፡ ፍለጋ
ይሰበር ፡ አልባስጥሮሴ
ከእግርህ ፡ ስር ፡ ሙሉ ፡ ማንነቴ
ይጠበው ፡ እግርህን ፡ እንባዬ
እንደ ፡ ውሃ ፡ ፊትህ ፡ ይፍሰስ ፡ ነፍሴ
ካንተ ፡ ውጪ ፡ እኔነ ፡ የለኝም
መሰዊያው ፡ ላይ ፡ ህኸው ፡ አለሁኝ
ብትወድ ፡ በሃይለኛው ፡ ንፋስህ
ብትወድ ፡ በነበልባል ፡ እሳት
ብትወድ ፡ ዝም ፡ ባለው ፡ ፀጥታ
ብትወድ ፡ በትንሿ ፡ ኮሽታ
ብቻ ፡ አንተ ፡ ና ፡ ብቻ ፡ አንተ ፡ ና
አንተ ፡ ብቻ ፡ ና ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ና
አልሰለችም ፡ አንተን ፡ መጠበቅ ፡ ቀንና ፡ ለሊት
አይደክመኝም ፡ እጠብቅሃለሁ ፡ ቀንና ፡ ለሊት
የዘላለም ፡ ረሃቤ ፡ ነህ ፡ የዘላለም ፡ እርካታዬ
አያረካኸኝ ፡ ምራብህ ፡ እየሞላኸኝ ፡ ምጠማህ
ከጎኔ ፡ ሆነህ ፡ ምናፍቅህ ፡ እየዳሰስከኝ ፡ ምራብህ
ከጎኔ ፡ ሆነህ ፡ ምናፍቅህ ፡ እየዳሰስከኝ ፡ ምራብህ
አተረፍኩ ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ስላልኩ ፡ አንተረፍኩ
አወኩበት ፡ አንተን ፡ ስለመረጥኩ ፡ አወኩበት
አተረፍኩ ፡ ክብሬ ፡ ስላረኩን ፡ አተረፍኩ
አወኩበት ፡ አንተን ፡ ስለወደድኩ ፡ አወኩበት
አስቀድሜ ፡ ፅድቅህን ፡ አስቀድሜ ፡ ፊትህን
አስቀድሜ ፡ ወደጏዳ ፡ አስቀድሜ ፡ በሬን ፡ ልዝጋ
መጀመሪያ ፡ ፅድቅህን ፡ መጀመሪያ ፡ ፊትህን
መጀመሪያ ፡ ወደጏዳ ፡ መጀመሪያ ፡ ላወጋህ
ፍለጋ ፡ ፍለጋ ፡ ፍለጋ
ቀኖቼ ፡ ይለቁ ፡ አንተን ፡ ፍለጋ
|