From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
ኦ ፡ ወዴ ፡ ስለምወድህ ፡ ስለምወድህ ፡ ሁለንተናዬ ፡ የኸውልህ
እየሱስ ፡ ወዴ ፡ ስለምወድህ ፡ ስለምወድህ ፡ ሁለንተናዬ ፡ የኸውልህ
ከቃላት ፡ ያለፈ ፡ ፍቅር
ዋጋን ፡ የሚያስከፍል ፡ መሰዋት
ይዤልህ ፡ ልምጣ ፡ እንደገና
ብቸኛውን ፡ ይሳቄን ፡ ልሰዋ
እራስህን ፡ በቃልኪዳንህ ፡ የሰጠኸኝ ፡ እንኳን
አይበልጥብኝም ፡ ካንተ ፡ እራስህ
አይተካልኝም ፡ አብሮነትህን
አልሸሽግም ፡ የልቤን ፡ ክፍሎች ፡ ወደሗላ
አልደብቅም ፡ በሬ ፡ ክፍት ፡ ነው ፡ ላንተ ፡ ጌታ
መርምረኝ ፡ የውስጠኛዬን ፡ ጠልቀህ ፡ እወቀው
ታደገኝ ፡ ብኩርናዬን ፡ እንዳልሸጠው
በመታዘዜ ፡ እንድወድህ
እድሜ ፡ ዘመኔን ፡ እንድገዛልህ
ኦ ፡ ወዴ ፡ ስለምወድህ ፡ ስለምወድህ ፡ ሁለንተናዬ ፡ የኸውልህ
እየሱስ ፡ ወዴ ፡ ስለምወድህ ፡ ስለምወድህ ፡ ሁለንተናዬ ፡ የኸውልህ
መሰዋቴን ፡ ላዘጋጅልህ ፡ እንዳዘዝከኝ
ቢሸከምም ፡ የተስፈዬን ፡ ቃሌ ፡ ራስህ ፡ የሰጠኸኝ
አልቆጥረውም ፡ የምድረኛውን ፡ ዋና ፡ አድርጌ
ርስቴ ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ሌላው ፡ አይጎድለኝ ፡ ቢወጣ ፡ ከእጄ
ብቻ ፡ ጌታዬ ፡ ደስ ፡ ይበልህ ፡ ሁለንተናዬ ፡ ያገልግልህ
ብቻ ፡ ጌታዬ ፡ ደስ ፡ ይበልህ ፡ ሁለንተናዬ ፡ ያገልግልህ
ኦ ፡ ወዴ ፡ ስለምወድህ ፡ ስለምወድህ ፡ ሁለንተናዬ ፡ የኸውልህ
እየሱስ ፡ ወዴ ፡ ስለምወድህ ፡ ስለምወድህ ፡ ሁለንተናዬ ፡ የኸውልህ
ከቃላት ፡ ያለፈ ፡ ፍቅር
ዋጋን ፡ የሚያስከፍል ፡ መሰዋት
ይዤልህ ፡ ልምጣ ፡ እንደገና
ብቸኛውን ፡ ይሳቄን ፡ ልሰዋ
|