From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
|
|
ህሊና ፡ ካሳሁን (Hillina Kassahun)
|
|
|
|
፫ (3)
|
አልበም (linurilih)
|
| ቁጥር (Track):
|
፰ (8)
|
| ርዝመት (Len.):
|
7:19
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
|
የህሊና ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች (Albums by Hillina Kassahun)
|
|
"" has no sub pages.
|
አልለምደውም
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
እግዚአብሄር ፡ ሰው ፡ ሆኖ ፡ ከዙፉኑ ፡ መውረዱ
ዛሬም ፡ ትኩስ
ይሄን ፡ ስጋ ፡ ለብሶ ፡ ራሱን ፡ ማዋረዱ
ዛሬም ፡ ትኩስ
ሞትና ፡ ትንሳኤው ፡ ዛሬም ፡ ትኩስ
የፈሰሰው ፡ ደሙ ፡ ዛሬም ፡ ትኩስ
የመስቀል ፡ ትግሉ ፡ ዛሬም ፡ ትኩስ
በእኔ ፡ ውስጥ ፡ ማደሩ ፡ ዛሬም ፡ ትኩስ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
አልለምደውም ፡ አልንቀውም
አልረሳውም ፡ አላቀለውም
አልለምደውም ፡ አልንቀውም
አልረሳውም ፡ አላቀለውም
ተአምር ፡ ነው ፡ ተአምር ፡ ነው ፡ ተአምር ፡ ነው
የሄድክበት ፡ ርቀት ፡ እርቅን ፡ ለመፈጸም
ተአምር ፡ ነው
ፍቅርህን ፡ ለመግለጽ ፡ መንፈስህን ፡ ለማፍሰስ
ተአምር ፡ ነው
ተአምር ፡ ነው ፡ ተአምር ፡ ነው ፡ ተአምር ፡ ነው
የሄድክበት ፡ ርቀት ፡ እርቅን ፡ ለመፈጸም
ተአምር ፡ ነው
ፍቅርህን ፡ ለመግለጽ ፡ መንፈስህን ፡ ለማፍሰስ
ተአምር ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
አልለምደውም ፡ አልንቀውም
አልረሳውም ፡ አላቀለውም
አልለምደውም ፡ አልንቀውም
አልረሳውም ፡ አላቀለውም
ገና ፡ አለማት ፡ ሳይፈጠር ፡ በራስህ ፡ ውስጥ
ያለ ፡ ነውር ፡ ያለ ፡ እንከን
ንጹሕ ፡ አድርገህ ፡ በአብ ፡ ፊት ፡ ያቀረብከን
አንዲች ፡ ሀጥያት ፡ እንኳን ፡ ሳትሰራ
መሰዋትነትህን ፡ ቀድመህ ፡ ያፀናህ
ጊዜው ፡ ሲደርስ ፡ የትግሉ
አይንህን ፡ አትኩረህ ፡ ወደ ፡ መስቀሉ
ፍንክች ፡ እንኳን ፡ ሳትል ፡ ቀኝና ፡ ግራ
መራራውን ፡ ጽዎ ፡ ለአንዴ ፡ የጠጣህ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
አልለምደውም ፡ አልንቀውም
አልረሳውም ፡ አላቀለውም
አልለምደውም ፡ አልንቀውም
አልረሳውም ፡ አላቀለውም
በአብ ፡ ቀኝ ፡ በራስህ ፡ ውስጥ ፡ አስቀምጠህ
የልጅነት ፡ መብትን ፡ ስልጣን
አባ ፡ ምልበት ፡ ድፍረትን ፡ አጎናፅፈህ
ወደ ፡ ፀጋህ ፡ ዙፋን ፡ ስር ፡ በነጻነት
እንድቀርብ ፡ ሆነልኝ ፡ ክብርህ ፡ ባለበት
ዛሬም ፡ በፀጋህ ፡ ስመላለስ
እባብና ፡ ጊንጡን ፡ እየረጋገጥኩ
አውቃለሁ ፡ አንዳችም ፡ ከእኔ ፡ እንዳልሆነ
ከሞት ፡ ያስነሳህ ፡ መንፈስ ፡ በእኔ ፡ እንዳደረ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
አልለምደውም ፡ አልንቀውም
አልረሳውም ፡ አላቀለውም
አልለምደውም ፡ አልንቀውም
አልረሳውም ፡ አላቀለውም
ያንተ ፡ ሽታ ፡ ለሚጠፉት ፡ ነው ፡ የሞት ፡ መአዛ
ለሚድኑት ፡ ግን ፡ የህይወት ፡ እፎይታ
ለሚድኑት ፡ ግን ፡ የህይወት ፡ እፎይታ
ያንተ ፡ ሽታ ፡ ለሚጠፉት ፡ ነው ፡ የሞት ፡ መአዛ
ለሚድኑት ፡ ግን ፡ የህይወት ፡ እፎይታ
ለሚድኑት ፡ ግን ፡ የህይወት ፡ እፎይታ
|