መሰውያዬ (Mesewyaye) - ህሊና ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ህሊና ፡ ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

፫
(3)

Linurilih
(Linurilih)

ቁጥር (Track):

፪ (2)

ርዝመት (Len.): 8:18
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

"" has no sub pages.

ወደ ፡ ቤተል ፡ መጀመርያ ፡ ወዳወቁህ ፡ ስፍራ ፡ እመለሳለሁ
ቃል ፡ ኪዳኔን ፡ አድሳለሁ

ህያውን ፡ መስዋዕት ፡ ሰውነቴን ፡ በፊትህ ፡ አቀርባለሁ
ከእንግዲ ፡ መኖርያዬ ፡ እዚሁ ፡ ነው ፡ በቤተል ፡ ነው
ከእንግዲ ፡ ማደርያዬ ፡ እዚህ ፡ ነው ፡ በልፍኝህ ፡ ነው

መሰውያዬ ፡ ዘላለም ፡ በፊትህ ፡ እሳት ፡ ይኑረው
ያርግ ፡ ወደማደሪያህ ፡ እጣኑን ፡ አሽትተው
ደስ ፡ ያሰኝህ ፡ ልብህን ፡ ያርካው ፡ መቅደስህን ፡ ይሙላው/2

ሰውነቴ ፡ ድኖ ፡ ቀረ ፡ አልለቅ ፡ ህም ፡ ብዬ ፡ የባረከኝ ፡ ለታ
ቅብዝብህ ፡ ነፍሴ ፡ በእጅህ ፡ ተዳሳ/2

በጥልቁ ፡ ፍቅርህ ፡ ለአንዴና ፡ ለመጨረሻ ፡ ተማርካ
ዘወትር ፡ ትጠብቃለች ፡ አንተን ፡ ተርባ
በየለት ፡ ትጠራሃለች ፡ አንተን ፡ ተርባ
ዘወትር ፡ ትጠብቃለች ፡ አንተን ፡ ተርባ
በየለት ፡ ትጠራሃለች ፡ አንተን ፡ ተርባ

መሰውያዬ ፡ ዘላለም ፡ በፊትህ ፡ እሳት ፡ ይኑረው
ያርግ ፡ ወደማደሪያህ ፡ እጣኑን ፡ አሽትተው
ደስ ፡ ያሰኝህ ፡ ልብህን ፡ ያርካው ፡ መቅደስህን ፡ ይሙላው/2

እኔና ፡ ቤቴ ፡ ዘር ፡ ማንዘሬ ፡ ልንከተልህ ፡ ልንገዛልህ
እንቀድሳለን ፡ ማዳሪያችንን ፡ ለንጉሳችን
አንተን ፡ ሚመጥን ፡ ልብህን ፡ ሚያረካ ፡ የሚያስደስትህ
ይሁንልህ ፡ ሁለንተናችን ፡ ይሁንልህ ፡ ስውርጏዳችን

ሁሉ ፡ ባንተ ፡ ላንተ ፡ ካንተ ፡ ነው/6