ጣልቃ ፡ ሲገባ (Talka Sigeba) - ህሊና ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ህሊና ፡ ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

፫
(3)

አልበም
(linurilih)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 7:51
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

"" has no sub pages.

ጣልቃ ፡ ሲገባ

እግዚአብሄር ፡ ጣልቃ ፡ ሲገባ ፡ እጁ ፡ ሲነሳ
ማነው ፡ ሚረዳ ፡ ማነው ፡ ሚያስረዳ
ማነው ፡ ሚረዳ ፡ ማነው ፡ ሚያስረዳ
እግዚአብሄር ፡ ጣልቃ ፡ ሲገባ ፡ እጁ ፡ ሲሰራ
ማነው ፡ ሚረዳ ፡ ማነው ፡ ሚያስረዳ
ማነው ፡ ሚረዳ ፡ ማነው ፡ ሚያስረዳ
የዘመናትን ፡ ጥያቄ ፡ በአንዲት ፡ ለሊት
የእድሜ ፡ ዘመን ፡ ቋጠሮ ፡ በአንድ ፡ ሰከንድ
አየን ፡ ሲፈታ ፡ አየን ፡ ሲፈታ
የዘመናትን ፡ ጥያቄ ፡ በአንዲት ፡ ለሊት
የእድሜ ፡ ዘመን ፡ ቋጠሮ ፡ በአንድ ፡ ሰከንድ
አየን ፡ ሲፈታ ፡ አየን ፡ ሲፈታ
አየን ፡ ሲፈታ ፡ አየን ፡ ሲፈታ

ርህራሄህ ፡ ቸርነትህ ፡ አያልቅምና ፡ አያልቅምና
የሰው ፡ ልጆች ፡ ሁሉ ፡ መጡ ፡ ወዳንተ
እረፍት ፡ ፍለጋ ፡ እረፍት ፡ ፍለጋ
ርህራሄህ ፡ ምህረትህ ፡ አያልቅምና ፡ አያልቅምና
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ መጡ ፡ ወዳንተ
ህይወት ፡ ፍለጋ ፡ ህይወት ፡ ፍለጋ
የሰራዊት ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ አንተ ፡ ስራ
በአምላክረት ፡ በክብርህ ፡ ፊትህ ፡ ያብራ
ፊትህ ፡ ያብራ ፡ ፊትህ ፡ ያብራ
ጣልቃ ፡ ግባ ፡ ጣልቃ ፡ ግባ
የሰራዊት ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ አንተ ፡ ስራ
በአምላክረት ፡ በክብርህ ፡ ፊትህ ፡ ያብራ
ፊትህ ፡ ያብራ ፡ ፊትህ ፡ ያብራ
ጣልቃ ፡ ግባ ፡ ጣልቃ ፡ ግባ

ይህቺ ፡ እማ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ጣት ፡ ናት
ይህቺ ፡ እማ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ክንድ
የሚያስብልን ፡ ተአምራት ፡ ስታደርግ ፡ በምህረትህ
ሰምተው ፡ መጡ ፡ ዙሪያዬ ፡ ያሉ ፡ ሁሉ
አላዛሬን ፡ ሊጎበኙ
የሸተተው ፡ የገነዝኩት ፡ ቆሞ ፡ ሲሄድ ፡ በድንገት
ይህቺ ፡ እማ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ጣት ፡ ናት
ይህቺ ፡ እማ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ክንድ
የሚያስብልን ፡ ተአምራት ፡ ስታደርግ ፡ በምህረትህ
ሰምተው ፡ መጡ ፡ ዙሪያዬ ፡ ያሉ ፡ ሁሉ
አላዛሬን ፡ ሊጎበኙ
የሸተተው ፡ የገነዝኩት ፡ ቆሞ ፡ ሲሄድ ፡ በድንገት
ሙታን ፡ የሚታዘዙለት ፡ ስላስነሳው
ሙታን ፡ አቤት ፡ የሚሉት ፡ ስለጠራው
ሙታን ፡ የሚታዘዙለት ፡ ስላስነሳው
ሙታን ፡ አቤት ፡ የሚሉት ፡ ስለጠራው

ርህራሄህ ፡ ቸርነትህ ፡ አያልቅምና ፡ አያልቅምና
የሰው ፡ ልጆች ፡ ሁሉ ፡ መጡ ፡ ወዳንተ
እረፍት ፡ ፍለጋ ፡ እረፍት ፡ ፍለጋ
የሰራዊት ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ አንተ ፡ ስራ
በአምላክረት ፡ በክብርህ ፡ ፊትህ ፡ ያብራ
ፊትህ ፡ ያብራ ፡ ፊትህ ፡ ያብራ
ጣልቃ ፡ ግባ ፡ ጣልቃ ፡ ግባ

ከባርነት ፡ ከእድሜ ፡ ልክ ፡ እስር
በአንድ ፡ ቀን ፡ ዮሴፍ ፡ ሲነግስ
በእኔ ፡ እርዳታ ፡ በእኔ ፡ ማገዝ
እዚህ ፡ ደርሳል ፡ ማንስ ፡ ሊል
የማንም ፡ እጅ ፡ ያልተባበረበት
እግዚአብሔር ፡ ብቻውን ፡ ያለበት
ሆኖ ፡ ፀና ፡ ግሩም ፡ ተአምር
እስከ ፡ ዛሬ ፡ ነው ፡ ምስክር
ከልጅነት ፡ የጠራውን ፡ ተማምኖበት
ህልሙን ፡ የሰጠውን ፡ ጌታ ፡ ተወራርዶበት
ከልጅነት ፡ የጠራውን ፡ ተማምኖበት
ህልሙን ፡ የሰጠውን ፡ ጌታ ፡ ተወራርዶበት

የህይወቴ ፡ በሮች ፡ ሁሉ ፡ ክፍት ፡ ናቸው ፡ ለንጉሱ
ለንጉሱ ፡ በሮች ፡ ይከፈቱ ፡ ለንጉሱ ፡ ደጆች ፡ ይከፈቱ
የህይወቴ ፡ በሮች ፡ ሁሉ ፡ ክፍት ፡ ናቸው ፡ ለንጉሱ
ለንጉሱ ፡ በሮች ፡ ይከፈቱ ፡ ለንጉሱ ፡ ደጆች ፡ ይከፈቱ