ፀሎቴ (Tselote) - ህሊና ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ህሊና ፡ ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

፫
(3)

አልበም
(linutilih)

ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 6:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

"" has no sub pages.

ፀሎቴ

እኔ ፡ ምለው ፡ ማንነት ፡ እንዳይኖረኝ
የምኖረው ፡ ህይወት ፡ ያንተ ፡ እንዲሆንልኝ
ይሄ ፡ ነው ፡ ፀሎቴ ፡ የየእለትም ፡ ምልጃዬ
የተሰበርን ፡ መንፈስ ፡ ባንተ ፡ ምትደገፍም ፡ ነፍስ
ሚገዛልህ ፡ ስጋን ፡ ጌታዬ ፡ ስጠኝ
እኔ ፡ ምለው ፡ ማንነት ፡ እንዳይኖረኝ
የምኖረው ፡ ህይወት ፡ ያንተ ፡ እንዲሆንልኝ
ይሄ ፡ ነው ፡ ፀሎቴ ፡ የየእለት ፡ ምልጃዬ
የተሰበርን ፡ መንፈስ ፡ ባንተ ፡ ምትደገፍም ፡ ነፍስ
ሚገዛልህ ፡ ስጋን ፡ ጌታዬ ፡ ስጠኝ

የጏዳዬን ፡ የስውሩን ፡ ማንም ፡ ሳይኖር ፡ ምኖረውን
ቀድስልኝ ፡ በመንፈስህ ፡ እጠብል
ሰው ፡ ማያየው ፡ ማያውቀውን
በሀሳቤ ፡ ሚቀመጠውን
እንደ ፡ ቃልህ ፡ እንደ ፡ ባህሪህ ፡ አድርግልኝ
አድርግልኝ ፡ ቀድስልኝ
አድርግልኝ ፡ ቀድስልኝ

ከቃላት ፡ ያለፈ ፡ ስር ፡ የሰደደ ፡ ለውጥ
የስጋን ፡ ፈቃድ ፡ ቸንክሮ ፡ የሚሰቅል
በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፍሬም ፡ የሚትረፈረፍ
ለሰው ፡ ልጆች ፡ የሚቆረስ ፡ ለብዙዋችም ፡ የሚተርፍ
እንደተጻፈልኝ ፡ ጌታዬ ፡ አርገኝ

የጏዳዬን ፡ የስውሩን ፡ ማንም ፡ ሳይኖር ፡ ምኖረውን
ቀድስልኝ ፡ በመንፈስህ ፡ እጠብል
ሰው ፡ ማያየው ፡ ማያውቀውን
በሀሳቤ ፡ ሚቀመጠውን
እንደ ፡ ቃልህ ፡ እንደ ፡ ባህሪህ ፡ አድርግልኝ
አድርግልኝ ፡ ቀድስልኝ
አድርግልኝ ፡ ቀድስልኝ

መስቀሌን ፡ ተሸክሜ ፡ እከተልሀለሁ
በጠባብዋ ፡ መንገድ ፡ ዛሬም ፡ እጎዛለሁ
እስካሳርፍ ፡ ድንኳኔን ፡ በአይኔ ፡ እስካይህ ፡ ጌታዬ
ትኩረቴ ፡ ሁሉ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ነው
ህይወቴን ፡ ላንተ ፡ እንድኖረው
አጋዠ ፡ መንፈስ ፡ ቅዲስ ፡ ዘወትር ፡ ቀባኝ

የጏዳዬን ፡ የስውሩን ፡ ማንም ፡ ሳይኖር ፡ ምኖረውን
ቀድስልኝ ፡ በመንፈስህ ፡ እጠብል
ሰው ፡ ማያየው ፡ ማያውቀውን
በሀሳቤ ፡ ሚቀመጠውን
እንደ ፡ ቃልህ ፡ እንደ ፡ ባህሪህ ፡ አድርግልኝ
አድርግልኝ ፡ ቀድስልኝ
አድርግልኝ ፡ ቀድስልኝ

ሰው ፡ ነፍሱን ፡ ሊያተርፍ ፡ ቢፈልጋት
አዋ ያገኛታል ፡ ላንተ ፡ ቢሰዋት
ሰው ፡ ነፍሱን ፡ ሊያድን ፡ ቢፈልጋት
አዋ ያገኛታል ፡ ላንተ ፡ ቢሰዋት
ላንተ ፡ ቢሰዋት ፡ ላንተ ፡ ቢሰዋት
ላንተ ፡ ቢሰዋት ፡ ላንተ ፡ ቢሰዋት
ሰው ፡ ነፍሱን ፡ ሊያተርፍ ፡ ቢፈልጋት
አዋ ያገኛታል ፡ ላንተ ፡ ቢሰዋት
ሰው ፡ ነፍሱን ፡ ሊያድን ፡ ቢፈልጋት
አዋ ያገኛታል ፡ ላንተ ፡ ቢሰዋት
ላንተ ፡ ቢሰዋት ፡ ላንተ ፡ ቢሰዋት
ላንተ ፡ ቢሰዋት ፡ ላንተ ፡ ቢሰዋት
ላንተ ፡ ቢሰዋት ፡ ላንተ ፡ ቢሰዋት
ላንተ ፡ ቢሰዋት ፡ ላንተ ፡ ቢሰዋት