መንገዴ ፡ ነህ (Mengede Neh) - ህሊና ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ህሊና ፡ ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

፫
(3)

አልበም
(linurilih)

ቁጥር (Track):

፬ (4)

ርዝመት (Len.): 5:16
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

"" has no sub pages.

መንገዴ ፡ ነህ

መፍትሄ ፡ ሲጠፉኝ ፡ መልሱ ፡ ሳይገባኝ
አይደለም ፡ ምጠራህ ፡ መውጫ ፡ ሲጠፋኝ
ሲነጋ ፡ ሲመሽ ፡ ድምፅህን ፡ መስማት
ተለማምጃለሁ ፡ ፊትህን ፡ መሻት
መፍትሄ ፡ ሲጠፉኝ ፡ መልሱ ፡ ሳይገባኝ
አይደለም ፡ ምጠራህ ፡ መውጫ ፡ ሲጠፋኝ
ሲነጋ ፡ ሲመሽ ፡ ድምፅህን ፡ መስማት
ተለማምጃለሁ ፡ ፊትህን ፡ መሻት

መንገዴ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ምርጫዬ
አማክርሀለሁ ፡ ጉዳዬን
ሌላስ ፡ የት ፡ ልሂድ ፡ ካንተ ፡ ውጪ
አለም ፡ የሚያስተምረው ፡ አይገባኝ
መንገዴ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ምርጫዬ
አማክርሀለሁ ፡ ጉዳዬን
ሌላስ ፡ የት ፡ ልሂድ ፡ ካንተ ፡ ውጪ
አለም ፡ የሚያስተምረው ፡ አይገባኝ

የራሴ ፡ አይደለሁም ፡ ከፍሎልኛል ፡ ዋጋውን
በማይረክስ ፡ ማይጠፉው ፡ በከበረው ፡ ደሙ
ታዲያ ፡ እንዴ ፡ ምን ፡ ይባላል ፡ ህይወቴ ፡ ነው ፡ ስለው
ከመፈጠሬ ፡ በፊት ፡ መሰዋት ፡ ለሆነው
የራሴ ፡ አይደለሁም ፡ ከፍሎልኛል ፡ ዋጋውን
በማይረክስ ፡ ማይጠፉው ፡ በከበረው ፡ ደሙ
ታዲያ ፡ እንዴ ፡ ምን ፡ ይባላል ፡ ህይወቴ ፡ ነው ፡ ስለው
ከመፈጠሬ ፡ በፊት ፡ መሰዋት ፡ ለሆነው

ያበጃጀኸኝ ፡ በራስህ ፡ አምሳል
እፍ ፡ ያልክብኝ ፡ ቅዱስ ፡ መንፈስህን
ማደርያህ ፡ እንድሆን ፡ የፍቅርህ ፡ አጋር
ቀድመህ ፡ ለየኸኝ ፡ ከፍጥረታት
መልአክቶቹ ፡ እንኳን ፡ ተገርመው
ሲመራመሩ ፡ የሰውን ፡ ልጅ ፡ አይተው
ምነኛ ፡ ይሆን ፡ የተወደድነው
ወልድ ፡ ከዙፉንህ ፡ ፈቅደህ ፡ የወረድከው
እውነትም ፡ ህይወት ፡ መንገድ ፡ ነኝ ፡ ያልከው
የአብን ፡ ፍቅር ፡ አንተ ፡ ተረከው
ለኔም ፡ ተስፉዬ ፡ እረፍቴ ፡ የሆንከው
እድሜ ፡ ዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ያንተ ፡ ነው

መንገዴ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ምርጫዬ
አማክርሀለሁ ፡ ጉዳዬን
ሌላስ ፡ የት ፡ ልሂድ ፡ ካንተ ፡ ውጪ
አለም ፡ የሚያስተምረው ፡ አይገባኝ

ሸክላው ፡ በሰሪው ፡ እጅ ፡ ውስጥ ፡ እንዳለው
ነው ፡ የኔ ፡ ህይወት ፡ ባንተ ፡ የተቃኘው
ከልጅነቴ ፡ በእቅፍህ ፡ አለሁ
እየመራኸኝ ፡ ፊትህን ፡ እያየሁ
መካሪዬ ፡ ነህ ፡ መሸሸጊያዬ
ሁሉን ፡ ምነግርህ ፡ ሚስጥረኛዬ
የግል ፡ የራሴ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱሴ
ብቸኛ ፡ ምርጫ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለኔ

መንገዴ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ምርጫዬ
አማክርሀለሁ ፡ ጉዳዬን
ሌላስ ፡ የት ፡ ልሂድ ፡ ካንተ ፡ ውጪ
አለም ፡ የሚያስተምረው ፡ አይገባኝ
መንገዴ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ምርጫዬ
አማክርሀለሁ ፡ ጉዳዬን
ሌላስ ፡ የት ፡ ልሂድ ፡ ካንተ ፡ ውጪ
አለም ፡ የሚያስተምረው ፡ አይገባኝ