From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
መንገድን ፡ ልጥረግልህ
ዘወትር ፡ ላጥንልህ ፡ በየልት ፡ ላጥንልህ
ላመቻች ፡ የልቤን ፡ ዙፋን
ንጉስ ፡ ሆይ ፡ እረፍ ፡ በእኔ ፡ ላይ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ስፈን ፡ በእኔ ፡ ላይ
ላስተናግድ ፡ መለኮትን
ደርሶ ፡ የለ ፡ ቀጠሮዋችን ፡ ደርሶ ፡ የለ ፡ ቀጠሮዋችን
እንግዳዬ ፡ እንግዳዬ
ከሩቅ ፡ ሰማሁኝ ፡ ኮቴህን ፡ እንግዳዬ
ቤቴን ፡ አወደው ፡ ሽታህ ፡ እንግዳዬ
ኢየሱሴ ፡ ኢየሱሴ
ለሊት ፡ ሰማሁኝ ፡ ድምፅህን ፡ ኢየሱሴ
ይኸው ፡ መጣሁኝ ፡ ስትል ፡ ኢየሱሴ
ናፍቆቴ ፡ ናፍቆቴ ፡ ና ፡ ክረም ፡ በቤቴ
ና ፡ ሰምብት ፡ በቤቴ ፡ ናፍቆቴ
ረድኤቴ ፡ መልህቄ ፡ ና ፡ ሰምብት ፡ በቤቴ
አልለቅህም ፡ ክረም ፡ በቤቴ ፡ መድሀኒቴ
በለሊት ፡ ሳሰላስልህ
በእንቅልፌም ፡ ደግሞ ፡ ሳልምህ
ፍቅርህ ፡ ልቤን ፡ ጎትቶት
ስጋዬ ፡ እንኳን ፡ አንተን ፡ ተርቦት
ሳሰናዳ ፡ አእምሮዬን
ስጠብቅህ ፡ እጅግ ፡ በጉጉት
መጣህልኝ ፡ እንደ ፡ ቃልህ
አገኘኸኝ ፡ እንደማልከው
በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሀሴት ፡ አድርጌ
ፊትህን ፡ ሳየው ፡ ተመኘሁ ፡ ዛሬ
ምነው ፡ እንደ ፡ ሄኖክ ፡ ብሻገረው
እጄን ፡ ይዘኸው ፡ ወደዛኛው
ምነው ፡ እንደ ፡ ሄኖክ ፡ ብሻገረው
እጄን ፡ ይዘኸው ፡ ወደዛኛው
እንግዳዬ ፡ እንግዳዬ
ከሩቅ ፡ ሰማሁኝ ፡ ኮቴህን ፡ እንግዳዬ
ቤቴን ፡ አወደው ፡ ሽታህ ፡ እንግዳዬ
ኢየሱሴ ፡ ኢየሱስዬ
ለሊት ፡ ሰማሁኝ ፡ ድምፅህን ፡ ኢየሱሴ
ይኸው ፡ መጣሁኝ ፡ ስትል ፡ ኢየሱሴ
ጠረንህ ፡ ቤቴን ፡ አውዶት
ህልውናህ ፡ አጥንቴን ፡ ተሰምቶት
የክብርህ ፡ ደመና ፡ ከቦኝ
ሙቀትህ ፡ ዙሪያዬን ፡ አቅፎኝ
በቅድስተ ፡ ቅዱሳንህ ፡ ውስጥ
ራሴን ፡ አገኘሁት ፡ ሳመልክ
ከቅዱሳን ፡ ጉባኤ ፡ ጋራ
በመንፈሴ ፡ ምስጋናን ፡ ሳሰማ
መልአክቶቹም ፡ ሲቀኙልህ
እኔም ፡ አጅቤ ፡ ሳለቅስ ፡ ሳዜም
የመፈጠሬን ፡ ትርጉም ፡ አግንቼ
ልቀር ፡ ጎጎሁኝ ፡ ለዘላለሜ
የመፈጠሬን ፡ ትርጉም ፡ አግንቼ
ልቀር ፡ ጎጎሁኝ ፡ ለዘላለሜ
መልአክቶቹም ፡ ሲቀኙልህ
እኔም ፡ አጅቤ ፡ ሳለቅስ ፡ ሳዜም
የመፈጠሬን ፡ ትርጉም ፡ አግንቼ
ልቀር ፡ ጎጎሁኝ ፡ ለዘላለሜ
የመፈጠሬን ፡ ትርጉም ፡ አግንቼ
ልቀር ፡ ጎጎሁኝ ፡ ለዘላለሜ
እንግዳዬ ፡ እንግዳዬ
ከሩቅ ፡ ሰማሁኝ ፡ ኮቴህን ፡ እንግዳዬ
ቤቴን ፡ አወደው ፡ መአዛህ ፡ እንግዳዬ
ኢየሱሴ ፡ ኢየሱሴ
ለሊት ፡ ሰማሁኝ ፡ ድምፅህን ፡ ኢየሱሴ
ይኸው ፡ መጣሁኝ ፡ ስትል ፡ ኢየሱሴ
ናፍቆቴ ፡ ናፍቆቴ ፡ ና ፡ ክረም ፡ በቤቴ
ና ፡ ሰምብት ፡ በቤቴ ፡ ናፍቆቴ ፡ ናፍቆቴ
ረድኤቴ ፡ መልህቄ ፡ ና ፡ ሰምብት ፡ በቤቴ
አልለቅህም ፡ ክረም ፡ በቤቴ ፡ መድሀኒቴ
አቤት ፡ ስወድህ ፡ ስቀርብህ ፡ ስወድህ
መቼም ፡ አልጠግብህ ፡ አልጠግብህ ፡ አልጠግብህ
ውዴ ፡ ስወድህ ፡ ስቀርብህ ፡ ስወድህ
ለዘላለም ፡ አልጠግብህ ፡ አልጠግብህ ፡ አልጠግብህ
አቤት ፡ ስወድህ ፡ ስቀርብህ ፡ ስወድህ
መቼም ፡ አልጠግብህ ፡ አልጠግብህ ፡ አልጠግብህ
ውዴ ፡ ስቀርብህ ፡ ስወድህ ፡ ስወድህ
ለዘላለም ፡ አልጠግብህ ፡ አልጠግብህ ፡ አልጠግብህ
|