አዲሱ ፡ መንገድ (Adisu Menged) - ኑኃሚን ፡ ተፈሪ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ኑኃሚን ፡ ተፈሪ
(Nuhamin Teferi)

፩
(1)

ልቀህ ፡ ታይ
(Likeh Tay)

ዓ.ም. (Year): 2026
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 3:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኑኃሚን ፡ ተፈሪ ፡ አልበሞች
(Albums by Nuhamin Teferi)

የሰውን ፡ ልጅ ደካማነት
እግዚአብሔር ፡ በመመልከት
አዲስ ፡ መንገድ ፡ ከፍቷል ፡ የሚዳንበት
ታላቅ ፡ የምስራች ፡ ለአለም ፡ ሁሉ ፡ የሚሆን
ከአምላክ ፡ ጋር ፡ ታረቁ ፡ በልጁ ፡ በማመን

እግዚአብሄር ፡ ቃል ፡ ስጋ ፡ ሆነ ፡ ለሁሉ ፡ አንዴ ፡ ለመሞት
በመስቀል ፡ ባፈሰሰው ፡ ደም ፡ ሊያነጻ የአለምን ፡ ሀጥያት
በሞትና ፡ በትንሳኤው ፡ በማዳኑም ፡ የሚያምኑ ፡ ሁሉ
በእርሱ ፡ በሆነው ፡ ቤዛነት ፡ እንዲያው ፡ በጸጋው ፡ ይጸድቃሉ

የአለምን ፡ ሁሉ ፡ ሃጥያት ፡ የሚያስወግድ ፡ የሚያድነው
ከእግዚአብሄር ፡ አብም ፡ የሚያደርሰው
አዲሱ ፡ መንገድ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
አዲሱ ፡ መንገድ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
አዲሱ ፡ ህይወት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

ከእግዚአብሄር ፡ ጋር ፡ ለመስማማት ፡ በልቡ ፡ የሚሻ ፡ ካለ
ሀጥያትም ፡ ከባድ ፡ ሸክም ፡ ሆኖበት ፡ የተቸገረ
ከታላቁም ፡ የአምላክ ፡ ቁጣ ፡ ለማምለጥ ፡ የሚወድ ፡ ቢኖር
ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ ፈጥኖ ፡ ይምጣ ፡ ወደሆነው ፡ የድነት ፡ በር

የአለምን ፡ ሁሉ ፡ ሃጥያት ፡ የሚያስወግድ ፡ የሚያድነው
ከእግዚአብሄር ፡ አብም ፡ የሚያደርሰው
አዲሱ ፡ መንገድ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
አዲሱ ፡ መንገድ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
አዲሱ ፡ ህይወት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው