ስላልፈቀድክልኝ ፡ አመሰግናለሁ (Slalfekedkilign Ameseginalehu) - ኑኃሚን ፡ ተፈሪ

ኑኃሚን ፡ ተፈሪ
(Nuhamin Teferi)

፩
(1)

ልቀህ ፡ ታይ
(Likeh Tay)

ዓ.ም. (Year): 2026
ቁጥር (Track):

፰ (8)

ርዝመት (Len.): 4:44
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኑኃሚን ፡ ተፈሪ ፡ አልበሞች
(Albums by Nuhamin Teferi)

ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ እግዚአብሄር ፡ መልካም ፡ ነው
ለክፉ ፡ እንዳትተወኝ ፡ ይህን ፡ አውቂያለሁ
ከእኔ ፡ ሀሳብ ፡ ይልቅ ፡ የአንተን ፡ እያፀናህ
ዛሬ ፡ የምደርስበት ፡ መንገዴን ፡ አቀናህ

ስለሆነ ፡ አንተ ፡ ያልከው
እጅግ ፡ ብዙ ፡ አትርፊያለሁ
አቆየኸኝ ፡ በጥበቃህ
አዘለቅኸኝ ፡ በምህረትህ

የለመንኳቸውን ፡ ሁሉ ፡ አልሰጠኸኝም
ለገዛ ፡ ፈቃዴ ፡ ፈጽሞ ፡ አልተውከኝም
መጥቶ ፡ የሚረባኝን ፡ ብቻ ፡ እያደረግህ
ከፊትህ ፡ አልጠፋሁም ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ማዳንህ

መከልከል ፡ በጊዜው ፡ ደስ ፡ ባያሰኝም
በጉዳት ፡ ከሚፈስ ፡ እንባ ፡ ግን ፡ አይበልጥም
ለበጎ ፡ ሆኖልኛል ፡ ዛሬ ፡ ላይ ፡ ሳስበው
ስላልፈቀድክልኝ ፡ አመሰግናለሁ

በሰው ፡ አይን ፡ ሲታይ ፡ እድል ፡ ከሚመስል
በአጅ ፡ የገባ ፡ እለት ፡ ግን ፡ ብዙ ፡ ከሚያጎድል
ረብ ፡ ከሌለው ፡ ነገር ፡ በመንገዴ ፡ ቆመህ
ከስንቱ ፡ ያስመለጥከኝ ፡ አምላኬ ፡ አንተ ፡ ነህ

መከልከል ፡ በጊዜው ፡ ደስ ፡ ባያሰኝም
በጉዳት ፡ ከሚፈስ ፡ እንባ ፡ ግን ፡ አይበልጥም
ለበጎ ፡ ሆኖልኛል ፡ ዛሬ ፡ ላይ ፡ ሳስበው
ስላልፈቀድክልኝ ፡ አመሰግናለሁ