የማንቀራረብ ፡ የማንቀላቀል
የማንፈላለግ ፡ የምንኖር ፡ በጥል
በነገድ ፡ በቋንቋ ፡ ልዩ ፡ ልዩ ፡ የነበርን
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ በደሙ ፡ አቃረበን
አሁን ፡ ወንድም ፡ እና ፡ እህቶች ፡ ተብለን
በአንድ ፡ መንግስት ፡ ውስጥ ፡ አብረን ፡ እንኖራለን
አንድ ፡ አካል ፡ የሆነ ፡ የቅዱሳን ፡ ህብረት
ተሰጥቶናል ፡ ሰላም ፡ ሆኖልናል ፡ ጥምረት
ከእንግዲህ ፡ አይሁድ ፡ የለም ፡ ወይም ፡ የግሪክ ፡ ሰው
ባሪያ ፡ ነው ፡ የሚባል ፡ ወይንም ፡ ነፃ ፡ ነው
በኢየሱስ ፡ አምነን ፡ ዳግም ፡ የተወለድን
ሁላችን ፡ በአንድነት ፡ የአግዚአብሄር ፡ ህዝቦች ፡ ነን
አንድ ፡ ነን ፡ በጌታ
አንድ ፡ ነን ፡ በኢየሱስ
ክርስቶስ ፡ የፀና ፡ መሰረት ፡ ሆነልን
እንገነባለን ፡ እየተናነጽን
ክፉ ፡ ምን ፡ ቢተጋ ፡ ችሎ ፡ የማያፈርሰው
በክርስቶስ ፡ የሆነ ፡ ህብረታችንን ፡ ነው
አንድ ፡ ነን ፡ በጌታ
አንድ ፡ ነን ፡ በኢየሱስ