የእግዚአብሄር ፡ ልጅ (Ye'egziabher Lij) - ኑኃሚን ፡ ተፈሪ

ኑኃሚን ፡ ተፈሪ
(Nuhamin Teferi)

፩
(1)

ልቀህ ፡ ታይ
(Likeh Tay)

ዓ.ም. (Year): 2026
ቁጥር (Track):

፬ (4)

ርዝመት (Len.): 5:16
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኑኃሚን ፡ ተፈሪ ፡ አልበሞች
(Albums by Nuhamin Teferi)

ክርስቶስ ፡ የህያው ፡ የእግዚአብሄር ፡ ልጅ ፡ ነህ
ይህንን ፡ አምኜ ፡ እኔም ፡ ተከተልኩህ

ብዙዎች ፡ በስህተት ፡ መንገድ ፡ ይገልጡሃል ፡ ይረዱሀል (ይገልጡሀል)
አንዳንዶች ፡ እንዲያውም ፡ ኤሊያስ ፡ ይሉሃል
ሌሎችም ፡ ከነብያት ፡ ከአንዱ ፡ ይመድቡሃል
እኔ ፡ ግን ፡ አንድ ፡ እውነት ፡ ህይወት ፡ በርቶልኛል

የሰው ፡ ልጅ ፡ በሀጥያት ፡ ታሞ ፡ ለዘመናት
አብ ፡ ለአለም ፡ የሰጠህ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ መድሀኒት
የምወደው ፡ ልጄ ፡ እርሱን ፡ ስሙት ፡ ያለው
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ አዎ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ ነው

አምናለሁ ፡ ከአብ ፡ እንደመጣህ
ብቸኛ ፡ መዳኛ ፡ እንደሆንህ
በአንተ ፡ ካልሆነ ፡ በስተቀር
አይቀርብም ፡ ማንም ፡ ወደ ፡ እግዚአብሄር

በአንተ ፡ ብቻ 2x
በአንተ ፡ ነው ፡ አለም ፡ የሚድነው