ደጋግሜ (Degagme) - ኑኃሚን ፡ ተፈሪ

ኑኃሚን ፡ ተፈሪ
(Nuhamin Teferi)

፩
(1)

ልቀህ ፡ ታይ
(Likeh Tay)

ዓ.ም. (Year): 2026
ቁጥር (Track):

፪ (2)

ርዝመት (Len.): 5:48
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኑኃሚን ፡ ተፈሪ ፡ አልበሞች
(Albums by Nuhamin Teferi)

ለወደድከኝ ፡ ከሀጥያቴም ፡ በደምህ ፡ ላጠብከኝ
ለአባትና ፡ ለአምላክህ ፡ ካህን ፡ እንድሆን ፡ ላረከኝ
ላንተ ፡ ክብር ፡ ይሁን

ከእግዚአብሄር ፡ ርቄ ፡ በሀጥያት
አቅም ፡ ሳጣ ፡ የምላቀቅበት
ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ቤዛነት ፡ ሆኖልኝ
ከዘለአለም ፡ ሞት ፡ አመለጥኩኝ

በፈሰሰው ፡ ደምህ ፡ አጥበኸኛልና
አንጽተህ ፡ ቀድሰህ ፡ ቀርቤያለሁና
ክበር ፡ እላለሁ ፡ እንደገና
ፊትህ ፡ እሆናለው ፡ ለምስጋና
ክበር ፡ እላለሁ ፡ ደጋግሜ
በምህረትህ ፡ ተገርሜ
በአንተ ፡ ይቅርታ ፡ ተገርሜ

በጨለማ ፡ የምመላለስ ሳለሁ1
ወደብርሀን ፡ መጠራት ፡ አገኘሁ
ለህይወቴ ፡ ደርሰህ ፡ በማዳንህ
በርቶልኛል ፡ የእውነት ፡ መንገድህ

ከቅዱሳን ፡ ጋራ ፡ ቆጥረኸኛልና
ህያው ፡ ተስፋን ፡ በአንተ ፡ አጊንቻለሁና
ክበር ፡ እላለሁ ፡ እንደገና
ፊትህ ፡ ቆማለሁ ፡ ለምስጋና
ክበር ፡ እላለሁ ፡ ደጋግሜ
በምህረትህ ፡ ተገርሜ