በቸርነቱ (Bechernetu) - ኑኃሚን ፡ ተፈሪ

ኑኃሚን ፡ ተፈሪ
(Nuhamin Teferi)

፩
(1)

ልቀህ ፡ ታይ
(Likeh Tay)

ዓ.ም. (Year): 2026
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 5:01
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኑኃሚን ፡ ተፈሪ ፡ አልበሞች
(Albums by Nuhamin Teferi)

በቸርነቱ
መልካሙም ፡ ሆነ ፡ ክፉውም ፡ ሆነ
ሀዘኑም ፡ ሆነ ፡ ደስታውም ፡ ሆነ
በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ አስችሎን
ዳግም ፡ ቆመናል ፡ ለክብሩ ፡ እንድንሆን

አማኑኤል ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ሆኖልናል ፡ እንዳንፈራ
ያንን ፡ ሁሉ ፡ ያሻገረን ፡ የምስጋና ፡ መዝሙር ፡ ሆነን

የእኛ ፡ ችሎታ ፡ የቱ ፡ ነው ፡ የቱስ ፡ አቅማችን
ዋስትና ፡ የሚሆን ፡ እስካሁን ፡ ስለመኖራችን
አንድም ፡ ተጨንቆ ፡ ቁመቱን ፡ ያረዘመ ፡ የለም
እንደ ፡ ፈቃዱ ፡ በፊቱ ፡ ይኖራል ፡ ሁሉም

በቸርነቱ ፡ ዘመናት ፡ ለሚያቀዳጀው
ለእግዚአብሄር ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ሀሌሉያ

ልመናችንን ፡ አልናቀ ፡ ጮኸን ፡ ስንጣራ
ህይወታችንን ፡ አዳናት ፡ ከጥፋት ፡ ጎዳና
ለጠላት ፡ ደስታ ፡ አልሰጠን ፡ እጁ ፡ አሳልፎ
ብርቱ ፡ አደረረገን ፡ በመልካም ፡ ክንዱ ፡ ደግፎ

በእኛ ፡ ላይ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ማዳን ፡ ገነነ
ገነነ ፡ ጥበቃው
ገነነ ፡ ምህረቱ
ገነነ ፡ ማዳኑ
ገነነ ፡ ብርታቱ