እንደ ፡ ቻልኩኝ ፡ ሆነህ ፡ ጉልበቴ
የቆምኩብህ የጸና ፡ ዓለቴ
የሚያየኝ ፡ ይወቅ ፡ እንደሆንክ ፡ ረዳት
እንደበዛልኝ ፡ የአንተ ፡ በጎነት
በህይወቴ ፡ ስለሆነው ፡ እያንዳንዱ ፡ ነገር
አምላኬ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ክብርን ፡ ተቀበል*2
በህይወቴ ፡ ስለሆነው ፡ እያንዳንዱ ፡ ነገር
አምላኬ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ክብርን ፡ ተቀበል*2
ስንቴ ፡ ምርኩዝ ፡ ሆንከኝ ፡ የምደግፍበት
ከድካም ፡ ዝለቴ ፡ የማንሰራበት
ሁሉን ፡ ከምትችለው ፡ ኃይልን ፡ ተቀብዬ
ያላለፍኩት ፡ የለም ፡ አቤቱ ፡ ጌታዬ
ሁሉን ፡ ከምትችለው ፡ ኃይልን ፡ ተቀብዬ
ያላለፍኩት ፡ የለም ፡ አቤቱ ፡ ጌታዬ
ክበር ፡ ክበር ፡ ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች
ብዙ ፡ ማዳን ፡ ምህረትህን ፡ ስላየች
ክበር ፡ ክበር ፡ ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች
በአንተ ፡ ብዙ ፡ በጎነትን ፡ ስላየች
ክበር ፡ ክበር ፡ ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች
የማይነጥፈው ፡ ምህረትህን ፡ ስላየች
ክበር ፡ ክበር ፡ ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች
በአንተ ፡ ብዙ ፡ ርህራሄን ፡ ስላየች
የመከራዬና ፡ የጭንቀቴን ፡ ጩኸት
ሰምተህ ፡ መልሰሃል ፡ ሆነኸኛል ፡ እረፍት
አምነው ፡ ለሚጠሩህ ፡ እንደማታሳፍር
ለደራሽነትህ እኔ ፡ አለው ፡ ምስክር
አምነው ፡ ለሚጠሩ ፡ እንደማታሳፍር
ለደራሽነትህ እኔ ፡ አለው ፡ ምስክር
ክበር ፡ ክበር ፡ ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች
ብዙ ፡ ማዳን ፡ ምህረትህን ፡ ስላየች
ክበር ፡ ክበር ፡ ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች
በአንተ ፡ ብዙ ፡ በጎነትን ፡ ስላየች
ክበር ፡ ክበር ፡ ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች
የማይነጥፈው ፡ ምህረትህን ፡ ስላየች
ክበር ፡ ክበር ፡ ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች
በአንተ ፡ ብዙ ፡ ርህራሄን ፡ ስላየች
ምህረትህን ፡ ስላያች ምህረትን ፡ ስላየች
በጎነትህን ፡ ስላያች በጎነትህን ፡ ስላየች
ምህረትህን ፡ ስላየች ምህረትን ፡ ስላየች
ርህራሄህን ፡ ስላየች ርህራሄህን ፡ ስላየች