እስቲ ፡ ወደማን (Esti Wedeman) - ኑኃሚን ፡ ተፈሪ

ኑኃሚን ፡ ተፈሪ
(Nuhamin Teferi)

፩
(1)

ልቀህ ፡ ታይ
(Likeh Tay)

ዓ.ም. (Year): 2026
ቁጥር (Track):

፭ (5)

ርዝመት (Len.): 5:30
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኑኃሚን ፡ ተፈሪ ፡ አልበሞች
(Albums by Nuhamin Teferi)

የማዳንህ ፡ እውነት ፡ ሳያጠራጥረን
ወደ ፡ ግራ ፡ ወደቀኝ ፡ አማራጭ ፡ ሳያምረን
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ አንተን ፡ እንከተላለን

ከላይ ፡ ከሰማያት ፡ የወረድህ ፡ መና
የነፍስን ፡ ረሀብ ፡ ጉድለት ፡ የምትሞላ
የህይወት ፡ እንጀራ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ
ዘለአለም ፡ ይኖራል ፡ ባንተ ፡ ያመነብህ

ጌታ ፡ ሆይ ፡ ካንተ ፡ ወደማን ፡ እንሄዳለን
ከቶ ፡ ወደማን ፡ እንሄዳለን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ካንተ ፡ ወደማን ፡ እንሄዳለን
እስቲ ፡ ወደማን ፡ እንሄዳለን
አውቀናል ፡ ደግሞም ፡ አምነናል ፡ ያላንተ ፡ የለም ፡ የሚያድን

አናፈገፍገም ፡ ከሰማነው ፡ ቃልህ
ከባርነት ፡ ቀንበር ፡ ካወጣን ፡ ከፍቅርህ
በአንተ ፡ እንኖራለን ፡ በእምነት ፡ በመጽናት
ለሁለንተናችን ፡ ሆነከናል ፡ ሙላት

ጌታ ፡ ሆይ ፡ ካንተ ፡ ወደማን ፡ እንሄዳለን
ከቶ ፡ ወደማን ፡ እንሄዳለን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ካንተ ፡ ወደማን ፡ እንሄዳለን
እስቲ ፡ ወደማን ፡ እንሄዳለን
አውቀናል ፡ ደግሞም ፡ አምነናል ፡ ያላንተ ፡ የለም ፡ የሚያድን

ሁሉን ፡ ትተን ፡ ተከትለንሃልበ 2x
የጣልነውን ፡ ዳግም ፡ አናነሳም
የያዝነውን ፡ እውነት ፡ አንረሳም
አብ ፡ ስቦናል እንድንከተልህ
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ዘለአለም ፡ ጌታ ፡ ነህ