አባት ፡ አለኝ (Abat Alegn) - ኑኃሚን ፡ ተፈሪ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ኑኃሚን ፡ ተፈሪ
(Nuhamin Teferi)

፩
(1)

ልቀህ ፡ ታይ
(Likeh Tay)

ዓ.ም. (Year): 2026
ቁጥር (Track):

፩ (1)

ርዝመት (Len.): 4:05
ጸሐፊ (Writer): ኑኃሚን ፡ ተፈሪ
(Nuhamin TeferiProperty "Writer" has a restricted application area and cannot be used as annotation property by a user.)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኑኃሚን ፡ ተፈሪ ፡ አልበሞች
(Albums by Nuhamin Teferi)

አባ ፡ ብዬ ፡ እንድጠራው ፡ ያደረገኝ
ልጄ ፡ ብሎ ፡ የሚጠራኝ ፡ የሚወደኝ
እርሱ ፡ አለልኝ ፡ የምለው ፡ የማሳየው
የሰማዩ ፡ አባቴ ፡ እግዚአብሄር ፡ ነው

መኖሪያዬን ፡ አድርጎት ፡ ቤቱ
መውጣት ፡ መግባቴ ፡ ነው ፡ በፊቱ
በእረፍት ፡ ውሀ ፡ ዘንድ ፡ ይመራኛል
ገበታን ፡ ያዘጋጅልኛል
በሞት ፡ ጥላ ፡ እንኳን ፡ መካከል ፡ ብሄድ
እርሱ ፡ ከእኔጋ ፡ አለ ፡ ልቤ ፡ አይርድ
ስጋት ፡ የሌለው ፡ ህይወት ፡ ሰጥቶኛል
በአባትነቱ ፡ አስተማምኖኛል

አለኝ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ አባት ፡ አለኝ
አለኝ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ የሚያኖረኝ
አባት ፡ ነለኝ ፡ የሚያኖረኝ
አባት ፡ አለኝ ፡ የሚያኖረኝ

ጎደለኝ ፡ አልል ፡ እርሱ ፡ እያለኝ
የሚያስፈልገኝን ፡ የሚያደርግልኝ
ለእንሰሶች ፡ ለእጽዋት ፡ ካሰበ
ለእኔ ፡ ያደርጋል ፡ የበለጠ
ከቶ ፡ አልጨነቅ ፡ በማየው ፡ ነገር
ከምስጋናጋ ፡ ከመንገር ፡ በቀር
በሀይሉ ፡ ችሎት ፡ እታመናለሁ
አባቴ ፡ የለም ፡ አንድም ፡ የሚሳነው

አለኝ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ አባት ፡ አለኝ
አለኝ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ የሚያኖረኝ
አባት ፡ አለኝ ፡ የሚያኖረኝ
አባት ፡ አለኝ ፡ የሚያኖረኝ