ማራናታ (Maranatha) - ኑኃሚን ፡ ተፈሪ

ኑኃሚን ፡ ተፈሪ
(Nuhamin Teferi)

፩
(1)

ልቀህ ፡ ታይ
(Likeh Tay)

ዓ.ም. (Year): 2026
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:39
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኑኃሚን ፡ ተፈሪ ፡ አልበሞች
(Albums by Nuhamin Teferi)

አንድ ፡ ደስታ ፡ አለን ፡ ውስጣችን ፡ የሞላን
ፈተና ፡ ቢበዛም ፡ ሁሌ ፡ የሚያጽናናን 2x
የዚች ፡ አለም ፡ ክፋት ፡ ቢያሰለቸንም
የተሰጠን ፡ ተስፋ ፡ ሚታጠፍ ፡ አይደለም
ኢየሱስ ፡ ይመጣል ፡ ደግሞም ፡ አይዘገይም
ናፍቆታችን ፡ እርሱን ፡ ያዳነንን ፡ ጌታ
ሁሌ ፡ እንለዋለን ፡ አሜን ፡ ማራናታ

እርሱ ፡ የሚኖርበት ፡ እኛም ፡ እንድንኖር
የተስፋን ፡ ቃል ፡ አለን ፡ መቶ ፡ እንደሚወስደን
ሰዎች ፡ እንዲድኑ ፡ ይታገሳል ፡ እንጂ
ቃሉን ፡ ይጠብቃል ፡ የእግዚአብሄር ፡ ልጅ

እኛስ ፡ አለን ፡ ተስፋ ፡ አዎ
የማይሻር ፡ የማይጠፋ ፡ አዎ
እኛስ ፡ አለን ፡ ርስት ፡ አዎ
ሁሉም ፡ አልፎ ፡ ምናርፍበት ፡ አዎ

በክርስቶስ ፡ የሞቱት ፡ ቀድመው ፡ ይነሳሉ
በህይወት ፡ የሚኖሩት ፡ ደግሞ ፡ ይነጠቃሉ
የሚለውን ፡ ቃሉን ፡ እንድናይ ፡ ሲፈጸም
ጽኑ ፡ ነው ፡ ልባችን አንጠራጠርም

እኛስ ፡ አለን ፡ ተስፋ ፡ አዎ
የማይሻር ፡ የማይጠፋ ፡ አዎ
እኛስ ፡ አለን ፡ ርስት ፡ አዎ
ሁሉም ፡ አልፎ ፡ ምናርፍበት ፡ አዎ

ማራናታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ና
እንላለን ፡ ናፍቀናልና