From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
ትውስ ፡ ድቅን ፡ ይልብኛል ፡ አይኔ ፡ ላይ
እየሱሴ ፡ መስቀሉ ፡ ላይ
የተወጋው ፡ ጎኑ ፡ ደሙ ፡ የፈሰሰው
እኔን ፡ ከሃጥያቴ ፡ ሊያጥበኝ ፡ ነው
የቆሰለም ፡ ጀርባው ፡ የተገረፈው
እኔን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ሊያስታርቀኝ ፡ ነው
እንዴት ፡ ነው ፡ የምትወደኝ/3
ምህረትህ ፡ ሰው ፡ አረገኝ
ደምህ ፡ ሲፈስልኝ ፡ በቀራንዮ ፡ ላይ
እርግማኔን ፡ ስትወስድ ፡ ስትሞት ፡ መስቀል ፡ ላይ
ያን ፡ ሁሉ ፡ አበሳ ፡ ለኔ ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ ነው
ማንም ፡ አላስገደደህ ፡ ፍቅር ፡ ይዞህ ፡ ነው/2
ፍቅርህ ፡ ያንተን ፡ ፍቅር ፡ እየሱስ
የትም ፡ አላየሁት ፡ ማንም ፡ ላይ ፡ አላየሁት
ልዩ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ/4
ባነበብኩት ፡ ብቻ ፡ አይደለም
በሰማሁት ፡ ብቻ ፡ አይደለም
ምህረትህ ፡ እየተከተለኝ
ስቀድቅ ፡ እርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ የሚያነሳኝ
ስደክም ፡ የሚያቆመኝ
አንተ ፡ መልካም ፡ አንተ ፡ መልካም ፡ ነህ
ኧረ ፡ አንተ ፡ መልካም ፡ አንተ ፡ መልካም ፡ ነህ
መልካም ፡ ነህ ፡ መልካም ፡ ነህ
አንተ ፡ መልካም ፡ ነህ
ክበርልኝ ፡ አንተ ፡ የኔ ፡ ጌታ
ክበርልኝ ፡ አንተ ፡ የኔ ፡ ወዳጅ/4
ትውስ ፡ ድቅን ፡ ይልብኛል ፡ አይኔ ፡ ላይ
እየሱሴ ፡ መስቀሉ ፡ ላይ
የተወጋው ፡ ጎኑ ፡ ደሙ ፡ የፈሰሰው
እኔን ፡ ከሃጥያቴ ፡ ሊያጥበኝ ፡ ነው
የቆሰለም ፡ ጀርባው ፡ የተገረፈው
እኔን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ሊያስታርቀኝ ፡ ነው
እንዴት ፡ ነው ፡ የምትወደኝ/3
ምህረትህ ፡ ሰው ፡ አረገኝ
|