ለዚህ ፡ ነው (Lezi New) - ሳምራዊት ፡ ሲዛር

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሳምራዊት ፡ ሲዛር
(Samrawit Sizar)

፪
(2)

Yene Aleme
(Yene Aleme)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፪ (2019)
ቁጥር (Track):

፱ (9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳምራዊት ፡ ሲዛር ፡ አልበሞች
(Albums by Samrawit Sizar)

ለዚ ፡ ነው ፡ መዘመር ፡ ያልተውኩት
ለዚ ፡ ነው ፡ አምልኮም ፡ ያልተውኩት
ለዚ ፡ ነው ፡ ተመስገን ፡ የምለው
እንዳንተ ፡ ስላላገኘው ፡ ነው

ለዚ ፡ ነው ፡ አምልኮ ፡ ያልተውኩት
ለዚ ፡ ነው ፡ መውደዴን ፡ ያልተውኩት
ለዚ ፡ ነው ፡ ተመስገን ፡ የምለው
እንዳንተ ፡ ስላላገኘው ፡ ነው

ተመችተኸኛል ፡ ከማንም ፡ በላይ
ውስጤን ፡ ያሳረፍካት ፡ አንተ ፡ አይደለህ ፡ ወይ
ተመችተኸኛል ፡ ከማንም ፡ በላይ
ነፍሴን ያሳረፍካት ፡ አንተ ፡ አይደለህ ፡ ወይ

ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ሰላም ፡ ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ደስታ
በዚ ፡ አለም ፡ አይደለም ፡ ነው ፡ እኮ ፡ በጌታዬ
በብርና ፡ በወርቅ ፡ የማይገዛውን
ሰላሙን ፡ ሰቶኛል ፡ በቃ ፡ ላምልከው
በብርና ፡ በወርቅ ፡ የማይገዛውን
ደስታውን ፡ ሰቶኛል ፡ እኔም ፡ ላምልከው

ገና ፡ አመልክሃለው/8

አይጨልምብህም ፡ አይነጋም ፡ ጠብቆ
አንተው ፡ ብርሃን ፡ ነህ ፡ ትገርማለህ ፡ እኮ

ሁሉም ፡ ነገር ፡ ባንተ ፡ እጅ ፡ ላይ ፡ ስላለ
አልፎ ፡ ያመልክሃል ፡ ባንተ ፡ የታመነ
ሁሉም ፡ ነገር ፡ ባንተ ፡ እጅ ፡ ላይ ፡ ስላለ
አልፎ ፡ ያመልክሃል ፡ አንተን ፡ የታመነ

አመክሃለው ፡ የኔ ፡ ወዳጅ ፡ አመልክሃለው/2

ገና ፡ አመልክሃለው/8

በዘመኔ ፡ የማልተወው ፡ የማላቆመው
እግዚአብሔርን ፡ የኔን ፡ ወዳጅ ፡ ማገልገሌን ፡ ነው
እግዚአብሔርን ፡ የኔን ፡ አባት ፡ ማገልገሌን ፡ ነው

በዘመኔ ፡ የማልተወው ፡ የማላቆመው
እግዚአብሔርን ፡ የኔን ፡ አባት ፡ ማገልገሌን ፡ ነው
እግዚአብሔርን ፡ የኔን ፡ ተስፋ ፡ ማገልገሌን ፡ ነው

ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ሰላም ፡ ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ደስታ
በዚ ፡ አለም ፡ አይደለም ፡ ነው ፡ እኮ ፡ በጌታ
በብርና ፡ በወርቅ ፡ የማይገዛውን
ሰላሙን ፡ ሰቶኛል ፡ በቃ ፡ ላምልከው
በብርና ፡ በወርቅ ፡ ያልተደገፈው
ደስታውን ፡ ሰቶኛል ፡ እኔም ፡ ላምልከው