እረኛዬ ፡ ነው (Eregnaye New) - ሳምራዊት ፡ ሲዛር

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሳምራዊት ፡ ሲዛር
(Samrawit Sizar)

፪
(2)

Yene Aleme
(Yene Aleme)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፪ (2019)
ቁጥር (Track):

፲ (10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳምራዊት ፡ ሲዛር ፡ አልበሞች
(Albums by Samrawit Sizar)

እግዚአብሔር ፡ እረኛዬ ፡ ነው
ሚያሳጣኝ ፡ የለም ፡ የማጣው ፡ የለም/2
እግዚአብሔር ፡ ፀጥታዬ ፡ ነው
ሚያውከኝ ፡ የለም/3

የማመልከው ፡ አምላክ ፡ የተደገፍኩት
ጠበቀኝ ፡ እንዳልጠፋ ፡ እኔ ፡ እንዳልሞት
በእጆቹ ፡ መዳፍ ፡ ላይ ፡ ስለቀረፀኝ
አልጠፋም ፡ የሚራራ ፡ አባት ፡ አለኝ

የማያስከፍል ፡ ቅጥር ፡ ሆኖኛል ፡ መተማመኛ
ማስፈራራቱ ፡ አያገኘኝም ፡ የዛ ፡ ቀማኛ
የሚጠብቀኝ ፡ የኔ ፡ አባት
አይሰለቸውም ፡ ቀንም ፡ ለሊት
የሚጠብቀኝ ፡ የኔ ፡ እረኛ
ቀኑን ፡ ጠብቆ ፡ ማታ ፡ ማይተኛ

በቀኜ ፡ ነህና ፡ እኔ ፡ አልደነግጥም
ሁልግዜ ፡ ስላማህ ፡ አልታወክም
ከመከራ ፡ ስጋት ፡ ልቤ ፡ እርፍ ፡ ብሏል
ህይወቴ ፡ በእጅህ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ምን ፡ ያስፈራኛል

የማያስከፍል ፡ ቅጥር ፡ ሆኖኛል ፡ መተማመኛ
ማስፈራራቱ ፡ አያገኘኝም ፡ የዛ ፡ ቀማኛ
የሚጠብቀኝ ፡ የኔ ፡ አባት
አይሰለቸውም ፡ ቀንም ፡ ለሊት
የሚጠብቀኝ ፡ የኔ ፡ እረኛ
ቀኑን ፡ ጠብቆ ፡ ማታ ፡ ማይተኛ

እኔ ፡ የምኖረው ፡ አንተን ፡ ታምኜ ፡ ነው/2
በህይወት ፡ የምኖረው ፡ ቃልህን ፡ ታምኜ ፡ ነው/2

እግዚአብሔር ፡ እረኛዬ ፡ ነው
ሚያሳጣኝ ፡ የለም ፡ የማጣው ፡ የለም/2
እግዚአብሔር ፡ ፀጥታዬ ፡ ነው
ሚያውከኝ ፡ የለም/3