From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
በየማለዳው ፡ ያንተ ፡ ውለታ
ይከተለኝ ፡ በጠላት ፡ እንዳልረታ
አይዞሽ ፡ ስትለኝ ፡ ስታስበኝ
ከአፌ ፡ መዝሙር ፡ እንዳይጠፋ ፡ አደረከኝ
ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ላድርግ ፡ ወዶኝ ፡ ነው ፡ ያለልክ/2
ዛሬ ፡ ዛሬስ ፡ ይገርመኛል
ሰው ፡ መሆኔ ፡ ይደንወኛል
ባለፍኩበት ፡ ጎዳናዬ
መከናወኔ ፡ ነው ፡ ጌታዬ
አሃሃ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ኦሆሆ ፡ ከፍ ፡ በል/2
አሃሃ ፡ ከፍ ፡ በል
ዛሬን ፡ ባንተ ፡ ካለፍኩ ፡ ነገን ፡ ምን ፡ እሆናለው
ክንድህ ፡ አስተማማኝ ፡ ተደግፌዋለው
ዛሬን ፡ ባንተ ፡ ካለፍኩ ፡ ነገን ፡ ምን ፡ እሆናለው
ቃልህ ፡ አስተማማኝ ፡ ተደግፌዋለው
ካላጣኸ ፡ ቦታ ፡ ካላጣኸው ፡ ልብ
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ወደድከኝ ፡ ገረመኝ ፡ ሳስብ
ማነው ፡ የወደደኝ ፡ ጠጋ ፡ ያረገኝ
ከመሞት ፡ አውጥቶ ፡ ፍቅር ፡ ያሳየኝ
ጌታ ፡ ነው/3 ጌታ
አንዴ ፡ በቻ ፡ አይደለም ፡ ብዙ ፡ ጊዜ ፡ ነው ፡ ጉልበት ፡ የሆንከኝ
እምነቴ ፡ ሲላላ ፡ ከጎኔ ፡ ቀመህ ፡ ያበረታኸኝ
መቼም ፡ መቼም ፡ መቼም ፡ ቢሆን ፡ አልረሳውም ፡ ያንተን ፡ ፍቅር
ሰው ፡ ያረክኝ ፡ ያወጣኸኝ ፡ ከጨለማው ፡ ከሞት ፡ ገደል/2
በየማለዳው ፡ ያንተ ፡ ውለታ
ይከተለኝ ፡ በጠላት ፡ እንዳልረታ
አይዞሽ ፡ ስትለኝ ፡ ስታስበኝ
ከአፌ ፡ መዝሙር ፡ እንዳይጠፋ ፡ አደረከኝ
ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ላድርግ ፡ ወዶኝ ፡ ነው ፡ ያለልክ/2
የኔማ ፡ ነገር ፡ የኔ ፡ ጉዳይ ፡ ተፈፀመልኝ ፡ ጎልጎታ ፡ ላይ
የኔማ ፡ ነገር ፡ የኔስ ፡ ጉዳይ ፡ ተፈፀመልኝ ፡ ጎልጎታ ፡ ላይ
መቼም ፡ መቼም ፡ መቼም ፡ ቢሆን ፡ አልረሳውም ፡ ያንተን ፡ ፍቅር
ሰው ፡ ያረክኝ ፡ ያወጣኸኝ ፡ ከጨለማው ፡ ከሞት ፡ ገደል/2
|