From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
እንዴት ፡ ይሆናል ፡ አልልም ፡ በቃ
ድንግል ፡ ፀንሳ ፡ ወልዳለች ፡ ለካ
እንዴት ፡ ይሆናል ፡ አልልም ፡ እኔ
ታምራት ፡ ህን ፡ ስላየው ፡ ባይኔ
አስቀድሜ ፡ ፅድቅህን ፡ ስፈልግ
አስቀድሜ ፡ መንግስትህን ፡ ስሻው
በረከትህ ፡ ፈልጎ ፡ አፈላልጎ
ካለሁበት ፡ መጣ ፡ ቤተን ፡ አውቆ
እንዴት ፡ ይሆናል ፡ አልልም ፡ በቃ
ድንግል ፡ ፀንሳ ፡ ወልዳለች ፡ ለካ
እንዴት ፡ ይሆናል ፡ አልልም ፡ እኔ
ታምራት ፡ ህን ፡ ስላየው ፡ ባይኔ
አስቀድሜ ፡ ፅድቅህን ፡ ስፈልግ
አስቀድሜ ፡ መንግስትህን ፡ ስሻው
በረከትህ ፡ ፈልጎ ፡ አፈላልጎ
ያለሁበት ፡ መጣ ፡ ቤተን ፡ አውቆ
አልልም ፡ አልልም ፡ አልልማ/3
አልልም ፡ አይሆንም ፡ አልልማ
አልልም ፡ አይችልም ፡ አልልም
ህልም ፡ ህልም ፡ እስኪመስለኝ ፡ ታምራት ፡ አርጎልኝ
መቁጠር ፡ ስለተሳነኝ ፡ እጄን ፡ ባፌ ፡ ጫንኩኝ
አከበረኝ ፡ አሃ ፡ አከበረኝ ፡ አሃ
ካፈር ፡ አንስቶ ፡ ኦሆ ፡ ሰው ፡ አረገኝ
ካንተ ፡ ከተነሳው ፡ ካለቀው ፡ አለም
ሰላም ፡ ነው ፡ ሚሰማኝ ፡ ጥያቄ ፡ የለም/3
እንዴት ፡ ይሆናል ፡ አልልም ፡ በቃ
ድንግል ፡ ፀንሳ ፡ ወልዳለች ፡ ለካ
እንዴት ፡ ይሆናል ፡ አልልም ፡ እኔ
ታምራት ፡ ህን ፡ ስላየው ፡ ባይኔ
አስቀድሜ ፡ ፅድቅህን ፡ ስፈልግ
አስቀድሜ ፡ መንግስትህን ፡ ስሻው
በረከትህ ፡ ፈልጎ ፡ አፈላልጎ
ያለሁበት ፡ መጣ ፡ ቤተን ፡ አውቆ
|