ቃልህ (Qaleh) - ሳምራዊት ፡ ሲዛር

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሳምራዊት ፡ ሲዛር
(Samrawit Sizar)

፪
(2)

Yene Aleme
(Yene Aleme)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፪ (2019)
ቁጥር (Track):

፯ (7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳምራዊት ፡ ሲዛር ፡ አልበሞች
(Albums by Samrawit Sizar)

አፀናኸ ፡ ልቤን ፡ ምንም ፡ እንዳይሆን
በፈተና ፡ ጎርፍ ፡ እንዳይወሰድ

ንፋሱ ፡ ነፍሶ ፡ ዝናቡም ፡ ዘንቦ
ህይወቴን ፡ ቤቴን ፡ አላፈረሰውም
ያምላኬ ፡ ቃሉ ፡ ልቦና ፡ ሰቶኝ
ቤቴን ፡ ባለት ፡ ላይ ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ ያሰራኝ

የተዘራውን ፡ ቃል ፡ አልበሉትም ፡ ወፎች
የሰማሁትን ፡ ቃል ፡ አልያዘውም ፡ እሾህ
በመንፈስ ፡ ታርሶ ፡ ነው ፡ የገባው ፡ ልቤ ፡ ውስጥ
በውሃ ፡ ዳር ፡ እንዳለ ፡ ዘፍ ፡ ፍሬው ፡ አይቋረጥ
በወንዝ ፡ ዳር ፡ እንዳለ ፡ ዘፍ ፡ ፍሬው ፡ አይቋረጥ

ቃልህ ፡ ይይዘኛል/4

ደክሜ ፡ እንዳልጠፋ ፡ ቃልህ ፡ ይይዘኛል/2
ደክሜ ፡ እንዳልጠፋ ፡ ቃልህ ፡ ይይዘኛል/2

በእጄ ፡ ቃል ፡ አለ ፡ በእጄ ፡ ላይ/3
አሸናፊ ፡ አረገኝ ፡ የበላይ

መልካም ፡ እድል ፡ የማይወሰድ
ከእግርስ ፡ በታች ፡ ጌታ ፡ መሆን
መልካም ፡ እድል ፡ የማይወሰድ
ከእግሮችህ ፡ ስር ፡ ሆና ፡ ቃልህን ፡ መማር

ይሁንልኝ ፡ ይሁንልኝ
የኔ ፡ አባት ፡ አንተው ፡ ምራኝ ፡ አስተምረኝ/2
ኦ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አንተ ፡ አውራኝ ፡ አስተምረኝ/2
ይሁንልኝ ፡ ይሁንልኝ
የኔ ፡ አባት ፡ አንተው ፡ ምራኝ/2
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አንተ ፡ አውራኝ ፡ አነጋግረኝ ፡ አስተምረኝ