የቅርቤ (yekerbe) - በረከት ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
በረከት ፡ ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

፫
(3)

መምህሩ
(Memheru)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2015/2023)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

ከሲዖል ፡ መውጣቴ ፡ ይበቃኝ ፡ ነበረ
በዚያ ፡ አላበቃም ፡ ፍቅሩ ፡ ጨመረ

ቀረበኝ ፡ አልሆንኩም ፡ ብቸኛ
አምላኬ ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ጓደኛ
ሳይዘው ፡ ሳይገድበው ፡ ትልቅነቱ
አብሮኝ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ትሁቱ

የቅርቤ ፡ ልበልህ ፡ የቅርቤ/2
ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ የቅርቤ
የቅርቤ ፡ ልበልህ ፡ የቅርቤ

ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ ይልቅ ፡ የቅርቤ ፡ ነህ
ፊትህን ፡ ተርቤ ፡ መቼ ፡ መቼ ፡ አጣሁህ
የሆድ ፡ የውስጤን ፡ ታውቀው ፡ የለም ፡ ወይ
ሳልተነፍስ ፡ ውዴ ፡ እየሱስ

ሰው ፡ ሚያውቀው ፡ ጉብዝናዬን
መቼ ፡ አየ ፡ ገመናዬን
ሸፍነኸው ፡ ጉድለቴን
ሚታየው ፡ ግን ፡ ሙላቴ

የቅርቤ ፡ ልበልህ ፡ የቅርቤ/2
ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ የቅርቤ
የቅርቤ ፡ ልበልህ ፡ የቅርቤ

ዞር ፡ ብዬ ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ መንገዴን ፡ ሳይ
የአንተ ፡ እንጂ ፡ የእኔ ፡ ኮቴ ፡ አይታይ
አባጣ ፡ ጎርባጣውን ፡ እኔ ፡ መውጣቴ
ይዘኸኝ ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ እናቴ
ምንም ፡ ባሳዝንህ ፡ በድካሜ
ታግሰኽ ፡ አቆምከኝ ፡ መድህኔ

ሰው ፡ ሚያውቀው ፡ ጉብዝናዬን
መቼ ፡ አየ ፡ ገመናዬን
ሸፍነኸው ፡ ጉድለቴን
ሚታየው ፡ ግን ፡ ሙላቴ

የቅርቤ ፡ ልበልህ ፡ የቅርቤ/2
ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ የቅርቤ
የቅርቤ ፡ ልበልህ ፡ የቅርቤ

በሰዎች ፡ መሐል ፡ ወይም ፡ ለብቻዬ
ድምፁን ፡ ያሰማኛል ፡ አብሮኝ ፡ ነው ፡ ጌታዬ
በዚህ ፡ ሂድ ፡ በዚያ ፡ ሂድ ፡ እያለኝ
ጠላት ፡ የማሰውን ፡ አለፍኩኝ
አምላኬ ፡ የመከረኝን
ሰምቼው ፡ አለፍኩኝ ፡ ስንቱን

የቅርቤ ፡ ልበልህ ፡ የቅርቤ/2
ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ የቅርቤ
የቅርቤ ፡ ልበልህ ፡ የቅርቤ

ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ ይልቅ ፡ የቅርቤ ፡ ነህ
ፊትህን ፡ ተርቤ ፡ መቼ ፡ መቼ ፡ አጣሁህ
የሆድ ፡ የውስጤን ፡ ታውቀው ፡ የለም ፡ ወይ
ሳልተነፍስ ፡ ውዴ ፡ እየሱስ

ሰው ፡ ሚያውቀው ፡ ጉብዝናዬን
መቼ ፡ አየ ፡ ገመናዬን
ሸፍነኸው ፡ ጉድለቴን
ሚታየው ፡ ግን ፡ ሙላቴ

የቅርቤ ፡ ልበልህ ፡ የቅርቤ/2
ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ የቅርቤ
የቅርቤ ፡ ልበልህ ፡ የቅርቤ