From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
በለሷን ፡ ፍሬዋን ፡ የጠበቀ
ይበላል ፡ ትግስቱ ፡ ያላለቀ
ጌታውን ፡ የጠበቀ ፡ ሰው
ስፍራዬን ፡ አለቅም ፡ ያለው
እሱ ፡ ሰው ፡ ከበረ ፡ አሄሄ ፡ ጌታን ፡ ያከበረ (2X)
ስምዖን ፡ ትጉህ ፡ እና ፡ ፃድቅ ፡ ሰው ፡ ነበረ
አያለው ፡ ቅዱሱን ፡ እያለ ፡ የኖረ
ሲጠብቅ ፡ ቆይቶ ፡ ህፃኑን ፡ ሲያየው
እጆቹን ፡ አንስቶ ፡ እንደዚህ ፡ አለዉ
ለህዝቦች ፡ ሁሉ ፡ መድኃኒት (2X)
የሆነውን ፡ እሱን ፡ ስላየሁት (2X)
መኖር ፡ አልሻም ፡ ውሰደኝ ፡ በቃ (2X)
በፅድቄ ፡ የኖርኩት ፡ እሱን ፡ ጥበቃ ፡ ልጁን ፡ ጥበቃ
ለኔ ፡ ስኬት (3X) ጌታን ፡ ማየት
ለኔ ፡ ከፍታ (3X) ፊትህ ፡ ነው ፡ ጌታ
ያርስ ፡ የለ ፡ ወይ ፡ በበጋ ፡ ልቡን ፡ ጥሎ
ገበሬው ፡ አምኖ ፡ ይዘንባል ፡ ብሎ
በደረቅ ፡ መሬት ፡ አምኖ ፡ ያረሰ
በክረምት ፡ እርሻው ፡ እረሰረሰ
እኔም ፡ እጠብቅሃለው
መውደዴን ፡ በዚ ፡ አሳይሃለው
አንድ ፡ ቀን ፡ ዓለም ፡ እያየህ
ልትወስደኝ ፡ ትመጣልኛለህ
ለኔ ፡ ስኬት...
ለኔ ፡ ከፍታ....
በለሷን.....
ፍፃሜው ፡ ክብር ፡ ነው ፡ አንተን ፡ መጠበቄ
መብራቴን ፡ አብርቼ ፡ ወገቤን ፡ ታጥቄ
እጠብቅሃለሁ ፡ እስክትመለስ
ሙሽራው ፡ አዳኜ ፡ ጌታዬ ፡ ኢሱስ
ፊትህን ፡ እንዳይ ፡ ተርቤ ፡ የለ ፡ ወይ ፡ እርቦኝ ፡ የለ ፡ ወይ
ለጥቂቶች ፡ ማዳን ፡ ብትዘገይ (2X)
ጨመረብኝ ፡ ፍቅርህ ፡ በየለቱ (2X)
ተናፍቀኃል ፡ ኢየሱስ ፡ የናዝሬቱ (2X)
እስክትመጣ ፡ እስክትመለስ
ጠብቅሃለው ፡ ውዴ ፡ ኢየሱስ
ጠነከተብኝ ፍቅርህ ፡ በረታ
በቶሎ ፡ ናልኝ ፡ የህይወቴ ፡ ጌታ
|