ማራናታ (Maranata) - በረከት ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
በረከት ፡ ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

፫
(3)

መምህሩ
(Memheru)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2015/2023)
ቁጥር (Track):

፭ (5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

የመምጣትህ ፡ ነገር ፡ የመጨረሻው
የነገርከን ፡ ትንቢት ፡ እየሆነ ፡ ነው
ናፍቆቱ ፡ አስባለኝ ፡ አሜን ፡ ማራናታ
ላይህ ፡ ጓጉቻለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ የኔ ፡ ጌታ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አትመጣም ፡ ወይ
የደማልኝን ፡ ጎንህን ፡ ልይ
አንተን ፡ ለማየት ፡ አይኖቼ ፡ ሻቱ
ቶሎ ፡ ናልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ የናዝሬቱ
ካንተ ፡ ጋር ፡ ልዋል ፡ ካንተ ፡ ጋር ፡ ልደር
እንደ ፡ ዮሐንስ ፡ በደረትህ ፡ ሥር
ደስታ ፡ የምለው ፡ ትልቁ ፡ እርካታዬ
አንተ ፡ ያለህበት ፡ ስኖር ፡ ነው ፡ ጌታዬ
በሌለህበት ፡ ከማገኝ ፡ ድሎት
ምድረበዳ ፡ ላይ ፡ ካንተ ፡ ጋር ፡ ልሰንብት
አንተን ፡ የማየት ፡ ናፍቆት ፡ ገባብኝ
እንደ ፡ ጓጓሁኝ ፡ መች ፡ እቀራለሁኝ

  ከአመፃ ፡ ብዛት ፡ ፍቅር ፡ ቀዘቀዘ
  ሰው ፡ ወንድሙን ፡ ገሎ ፡ መቼ ፡ ተወቀሰ
  አመፀኞች ፡ በዙ ፡ ክፋቱ ፡ ጨምሮ
  ተላልፈው ፡ ተሰጡ ፡ ለማይረባ ፡ አዕምሮ
  የድሆች ፡ ዳኛ ፡ የሁሉ ፡ አለቃ
  ና ፡ እና ፡ ከልክለው ፡ ለቅሶአችን ፡ ይብቃ
  የእናቶች ፡ እምባ ፡ ይላል ፡ ዋይ ፡ ዋይ
  ሩህሩህ ፡ ጌታ ፡ አትመጣም ፡ ወይ
  ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ተነሺ ፡ እና ፡ አብሪ
  ፍቅርን ፡ ለጣሉ ፡ እንዳትዘምሪ
  የገሃነም ፡ ደጅ ፡ ለካ ፡ ጥላቻ ፡ ነው
  ማይቋቋምሽ ፡ ሰይፍሽ ፡ ፍቅር ፡ ሲሆን ፡ ነው
  ጦር ፡ መሳሪያውን ፡ ፍቅር ፡ ያደረገ
  ጠላቱን ፡ ረቶ ፡ ወንድም ፡ አደረገ
  የሰው ፡ ጠባብ ፡ አፍ ፡ የሚጎርስ ፡ እህል
  ክፉ ፡ አንደበት ፡ አክሏል ፡ ሲዖል

    አትመጣም ፡ ወይ ፡ ማራናታ
አናርፍም ፡ ወይ ፡ ማራናታ (2X)

    ና ፡ ና ፡ ና ፡ ና ፡ ና ፡ ማራናታ (4X)
ሃሳዊ ፡ መምህራን ፡ ነብያቶች ፡ በዙ
ተናገረኝ ፡ ባዮች ፡ ለገንዘብ ፡ የተገዙ
ለታመመው ፡ ምስኪን ፡ እንግዳ ፡ ማረፊያ
በሽታው ፡ ሳያንሰው ፡ በፀሎት ፡ ሰበብ ፡ ዝርፊያ
ደምህ ፡ ተረግጦ ፡ ገንዘብ ፡ ገነነ
አንተን ፡ ያወቀ ፡ ሰው ፡ ክፉ ፡ ሆነ
ነዋይ ፡ ሚያፈቅር ፡ ትውልድ ፡ ተነሳ
ያረክለትን ፡ ምህረት ፡ የረሳ
ፈውሱ ፡ ለታይታ ፡ ለንግድ ፡ ቀረበ
በአዳኙ ፡ ስም ፡ ገንዘብ ፡ ተሰበሰበ
ገበያው ፡ ደርቶ ፡ በወንጌል ፡ ሰበብ
ስንቱን ፡ ታዘብነው ፡ አወይ ፡ ጉድ ፡ አጀብ
በሰጠው ፡ ፀጋ ፡ የሆነ ፡ ነጋዴ
በፍርድ ፡ ቀን ፡ የሚል ፡ ነው ፡ ወይኔ ፡ ጉዴ
መምጣቱ ፡ አይቀርም ፡ የእረኞች ፡ አለቃ
ስለበጎቹ ፡ የሚራራ ፡ ጠንቃቃ

  አትመጣም ፡ ወይ...
  ና ፡ ና...

ወደ ፡ ዓለም ፡ ሂዱ ፡ ወንጌልን ፡ ስበኩ
ነበር ፡ የተባልነው ፡ መስክሩ ፡ ታደጉ
ሰው ፡ ግን ፡ ካስማ ፡ ሰርቶ ፡ ወንበሯን ፡ ወደደ
መምህር ፡ እና ፡ ጌታ ፡ መባልን ፡ ለመደ
ወንጌል ፡ እንስራ ፡ አንቱታው ፡ ቀርቶ
ይሸለም ፡ የለ ፡ ወይ ፡ የሰራ ፡ ተግቶ
ከታበይንበት ፡ ዙፋናችን
እስኪ ፡ እንውረድ ፡ ለጌታችን
አላወጣንም ፡ አጋንንቶችን
አልፈወስንም ፡ ወይ ፡ በሽተኞችን
ጌታ ፡ በስምህ ፡ ብዙ ፡ አድርገን
አላውቃችሁም ፡ ስለምን ፡ አልከን
ከሚሉት ፡ ወገን ፡ እንዳይሆን ፡ ሂወቴ
መብራቴን ፡ ላብራ ፡ ሳይጎድል ፡ ዘይቴ
እስክተመጣልኝ ፡ ወይ ፡ እስክትወስደኝ
እየጠበኩህ ፡ እፀናለሁኝ

  ና ፡ ና...