አቤት ፡ ምህረትህ (Abet Mihretih) - በረከት ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
በረከት ፡ ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

፫
(3)

መምህሩ
(Memheru)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2015/2023)
ቁጥር (Track):

፫ (3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

አቤት ፡ ምህረትህ ፡ እንዴት ፡ ታላቅ ፡ ነው
መለኪያ ፡ የለው ፡ መስፈሪያ ፡ የለው ፡ እንዴት ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ እንደምን ፡ ታላቅ ፡ ነው
ያንት ፡ ምህረት ፡ ከማን ፡ ጋር ፡ ይስተያይ
ከፈጠርከው ፡ ፍጥረት ፡ ከምድር ፡ ወይ ፡ ሰማይ
የሚስተካከልህ ፡ ማን ፡ አለ ፡ በውኑ
አባቴ ፡ ምህረትህ ፡ ያክላል ፡ አንተኑ

  መለኪያ ፡ የለው ፡ መስፈሪያ ፡ የለው ፡ እንዴት ፡ ታላቅ (2X)
ሳይታዘዝ ፡ ጠላት ፡ እጅ ፡ ገብቶ
ሳምሶን ፡ ወደቀ ፡ ከመስመር ፡ ወጥቶ
ግን ፡ ምህረት ፡ ለምኖ ፡ መቼ ፡ አፈረ
የራሱ ፡ ፀጉር ፡ ማደግ ፡ ጀመረ
በህይወት ፡ ከሰራው ፡ በሞቱ ፡ ባሰ
ለዛ ፡ ኪዳን ፡ ሰው ፡ ምህረት ፡ ደረሰ
አንድ ፡ ዕድል ፡ ብቻ ፡ ባይለምንህ
ይኖር ፡ ነበረ ፡ በቸርነትህ
እንዴት ፡ እንዴት ፡ እንዴት ፡ ታላቅ ፡ ነው (2X) እንዴት ፡ ኧረ ፡ እንዴት
እንዴት ፡ እንዴት ፡ እንዴት ፡ ታላቅ ፡ ነው (2X) እንዴት ፡ ያንተ ፡ ምህረት

  አቤት ፡ ምህረትህ...
ብትጨምርለት ፡ አስራ ፡ አምስት ፡ ዓመት
ተዝቆ ፡ በማያልቅ ፡ ከሰፊ ፡ ምህረት
ከኖረበት ፡ ዕድሜ ፡ ከምህረትህ ፡ ወስዶ
አንተን ፡ ሳያከብር ፡ ጨረሰው ፡ በባዶ
እኔንም ፡ ገብቶኛል ፡ የቃልህ ፡ ዕውነት
ለካ ፡ ምዘምረው ፡ ባንተ ፡ ምህረት
መሃሪነትህን ፡ እዘምረዋለሁ
በጉልበቴ ፡ ሳይሆን ፡ በምህረት ፡ እኖራለሁ

  እንዴት...
  መለኪያ ፡ የለው...