መምህሩ (Memheru) - በረከት ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
በረከት ፡ ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

፫
(3)

መምህሩ
(Memheru)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2015/2023)
ቁጥር (Track):

፬ (4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

የሞተን ፡ በቃሉ ፡ የሚያነሳ
ደግሞም ፡ የሚፈውስ......
ሳይታይ ፡ ጠባሳ
ምስክር ፡ ለሚሻ ፡ እኔ ፡ አለሁ
በስሙ ፡ አምኜ ፡ ተፈውሻለሁ
እንኳን ፡ ፊቱ ፡ ያለሁቱ (እንኳን ፡ ስሙን ፡ ያመንኩቱ)
ዳኑ ፡ ከጀርባ ፡ የነኩቱ
ኢየሱስ ፡ ብሉ ፡ የተጣራ
በልቷል ፡ ፈውስን ፡ እንደ ፡ እንጀራ

       ፈውስን ፡ እንደ ፡ እንጀራ ፡ እንደ ፡ እንጀራ (2X)
ሀገር ፡ የሚያውቃት ፡ ከቤተ ፡ መቅደስ ፡ ስትመላለስ
ለፈውሷ ፡ ሳይሆን ፡ አምላኳን ፡ ወዳ ፡ ቀድማ ፡ የምትደርስ
ያሸማቀቃት ፡ ያስጎበጣትን ፡ ጀርባዋ ፡ ላይ
ይዛ ፡ ስትገባ ፡ ለካ ፡ ቀደሟታል ፡ ቅኖች ፡ የሚያይ

       ቢዳስሳት ፡ ጌታዋ
      ተፈወሰ ፡ ጀርባዋ
      ወደቀላት ፡ ቀንበሩ
      ስለመጣ ፡ መምህሩ
            አዳኝ ፡ መጥቷል ፡ መምህሩ
            ፍቅር ፡ መጥቷል ፡ መምህሩ
           ንጉስ ፡ መጥቷል ፡ መምህሩ
           ፈዋሽ ፡ መጥቷል ፡ መምህሩ

ደከመኝ ፡ ሳትል ፡ ተመላለሰች
ህመሟን ፡ ይዛ ፡ እቤቱ ፡ መጣች
ልክ ፡ እንደ ፡ ልማዷ ፡ ከምኩራብ ፡ ስትደርስ
የዛን ፡ ዕለት ፡ ሰባኪው ፡ መምህሩ ፡ ኢየሱስ

      ቢዳስሳት ፡ ጌታዋ
      ተፈወሰ ፡ ጀርባዋ
      ወደቀላት ፡ ቀንበሩ
      ስለመጣ ፡ መምህሩ
           አዳኝ ፡ መጥቷል ፡ መምህሩ
           ፈዋሽ ፡ መጥቷል ፡ መምህሩ
           ......... መጥቷል ፡ መምህሩ
                  ፍቅር ፡ መጥቷል ፡ መምህሩ (5X)

ልጅቷ ፡ ሞታለች ፡ አታድክም ፡ መምህሩን
ለወላጅ ፡ አባቷ ፡ ብለው ፡ አረዱት ፡ መርዶን
አትፍራ ፡ ብቻ ፡ እመን ፡ ሰምቶ ፡ አለው ፡ ጌታ
እቤታቸው ፡ ሄደ ፡ ባዛ ፡ ለቅሶ ፡ ጫጫታ
ተኛች ፡ እንጂ ፡ መች ፡ ሞተች
ቢላት ፡ ሳቁ ፡ ለቀስተኞች
ጌታ ፡ ወደ ፡ ውስጥ ፡ ገባና
ተነሽ ፡ አንቺ ፡ ብላቴና
በድኗ ፡ ልጅ ፡ ተነሳች
የጌታን ፡ ድምፅ ፡ ሰማች
ሙታን ፡ አቤት ፡ ሚሉት
ኢየሱስ ፡ የዓለም ፡ መድሃኒት

        እንኳን ፡ ፊቱን ፡ የጀርባውን ፡ ቀሚስ
        አይተው ፡ የለ ፡ ወይ ፡ የነካው ፡ ሲፈወስ
        አልዳነችም ፡ ወይ ፡ ያቺ ፡ ምስኪን
        በዕምነት ፡ ብትነካው ፡ ቀሚሱን

እንኳንስ ፡ ፊቱን ፡ ጀርባው ፡ መድኃኒት
አምኖ ፡ ለነካው ፡ የሚሰጥ ፡ ሂወት
የሚያገፋፋው ፡ አላማኝ ፡ መች ፡ ታጣ
በዕምነት ፡ ለነካች ፡ ከጀርባው ፡ ኃይል ፡ ወጣ

          ፈውስ ፡ እንደ ፡ እንጀራ.....
          እንኳን ፡ ፊቱ ፡ ያለሁቱ......

ይህን ፡ ወንጌል ፡ ያልሰማ ፡ እንዲሰማ
አውጃለሁ ፡ ከገጠር ፡ ከተማ
እንደሚያድን ፡ እንደሚታደግ
እሰብካለሁ ፡ ስለ ፡ እግዚአብሔር ፡ በግ
ያድናል ፡ የምለው ፡ እኔ
አድኖኝ ፡ ስላየሁ ፡ ባይኔ
ያድናል ፡ እኔ ፡ ያልኩት
አድኖኝ ፡ ስላየሁት

      ያድናል (8X)