አሜን ፡ አሜን (Amen Amen) - በረከት ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
በረከት ፡ ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

፫
(3)

መምህሩ
(Memheru)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2015/2023)
ቁጥር (Track):

፱ (9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

አሜን ፡ አሜን (16X)

ወንጌል ፡ ሲነገረኝ ፡ አትንገሩኝ ፡ ባይ
ጠንካራ ፡ ነበረ ፡ ልቤ ፡ እንደ ፡ ድንጋይ
ግን ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ጭንቀት ፡ ወደ ፡ ህይወቴ ፡ መጣ
ዕውቀት ፡ የመሰለኝ ፡ ምንም ፡ አላመጣ

ቢጨንቀኝ ፡ ቢጠበኝ ፡ ልሞክረው ፡ ብዬ
በስብከት ፡ ሞኝነት ፡ አሄ ፡ ይሁን ፡ አሜን ፡ ብዬ
አይቼ ፡ ማላውቀው ፡ የደስታ ፡ ካባ
ህይወቴ ፡ ለበሰ ፡ ኢየሱስ ፡ ሲገባ

ዛሬማ ፡ እሞትለታለሁ
ሂድ ፡ ቢለኝ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
እሱ ፡ ነው ፡ የመጨረሻዬ
አሜን ፡ ያልኩት ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ

አስገባሁት ፡ አሜን ፡ ልቤን ፡ ከፍቼ ፡ አሜን
ይኸው ፡ አለሁ ፡ አሜን ፡ ድኜ ፡ ቀርቼ ፡ አሜን
ያስገባሁት ፡ አሜን ፡ አሜን ፡ ብዬ ፡ አሜን
መድኃኒት ፡ ሆነኝ ፡ አሜን ፡ ኢየሱስዬ ፡ አሜን
    ኢየሱስዬ ፡ ውድዬ (4X)
      አሜን ፡ አሜን...

እንኳንስ ፡ ሊያቀርበኝ ፡ ሊገባ ፡ ከቤቴ
መጥራት ፡ ማይገባኝ ፡ ስሙን ፡ በአንደበቴ
ጌታ ፡ ግን ፡ ደግ ፡ ነው ፡ ምህረት ፡ የለበሰ
ለጠፋሁት ፡ ልጁ ፡ ፍቅርን ፡ ደገሰ

ፍርድ ፡ ነበረብኝ ፡ በሞት ፡ የሚያስቀጣ
የገዛ ፡ በደሌ ፡ ያመጣብኝ ፡ ጣጣ
ጌታ ፡ ግን ፡ ከፈለ ፡ የኃጢያቴን ፡ ዕዳ
አሜን ፡ በማለቴ ፡ ነውሬን ፡ አፀዳ

በኢየሱስ ፡ ህይወት ፡ አጊንቻለሁ
ልለየው ፡ እንዴት ፡ እችላለሁ
እስካይችል ፡ ይሄ ፡ ትከሻዬ
አይሏል ፡ ፍቅሩ ፡ በላዬ

አስገባሁት....
ኢየሱስዬ...
አሜን ፡ አሜን...

ከሰማይ ፡ ወረደ ፡ አሜን ፡ አሜን ፡ ደግሞ
ለእኔ ፡ ሞተ ፡ አሜን ፡ አሜን
ከሙታን ፡ ተነሳ ፡ አሜን ፡ አሜን
በክብር ፡ አረገ ፡ አሜን ፡ አሜን

ልክ ፡ እንደ ፡ መብረቅ ፡ አሜን ፡ አሜን
ከላይ ፡ እያበራ ፡ አሜን ፡ አሜን
ዳግም ፡ ይመለሳል ፡ አሜን ፡ አሜን
ከቅዱሳን ፡ ጋራ ፡ አሜን ፡ አሜን

ስምን ፡ ያተረፉ ፡ በየዘመናቸው
ተከታዮቻቸው ፡ ሲሞቱ ፡ ረሷቸው
ሁለት ፡ ሺ ፡ ዓመት ፡ ታሪክ ፡ ያልሸፈነው
ሰንጥቆ ፡ የመጣ ፡ የኢየሱሴ ፡ ስም ፡ ነው

ይኼን ፡ ስሰማ ፡ አሜን ፡ በማለቴ
ሰመረ ፡ ብርሃን ፡ በራ ፡ ቤቴ
አሜን ፡ በማለቴ (3X)
ሰመረ ፡ ሂወቴ
አሜን ፡ ያልኩት ፡ ጌታ (3X)
እስራቴን ፡ ፈታ