ለመልካም ፡ ሆነልኝ (lemelkam honelegn) - በረከት ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
በረከት ፡ ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

፫
(3)

መምህሩ
(Memheru)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2015/2023)
ቁጥር (Track):

፲ (10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

ለካ ፡ ይታለፋል ፡ ማይታለፈው
ከልኩ ፡ አያልፍም ፡ የሰው ፡ ፈተናው
ምጠፋ ፡ መስሎኝ ፡ ፈራች ፡ እንጂ ፡ ነፍሴ
ለካ ፡ ያስጨነከኝ ፡ ለጥቅሜ ፡ ለራሴ
በእሳት ፡ እያለፍኩ ፡ ስፈተን
ወርቅ ፡ አደረገው ፡ ህይወቴን
  ጌታ ፡ ሆይ ፡ አሁን ፡ ተማርኩ ፡ ተስተካከልኩ
  አመፃን ፡ ጥዬ ፡ ፅድቅንም ፡ ያዝኩ
  ያ ፡ ልፍስፍሱ ፡ ጠነከረ ፡ እንጂ ፡ ልቤ
  አላጠፋኝም ፡ የጋለው ፡ ከአጠገቤ
  ተስማምቶ ፡ የኖረ ፡ ከአፈር ፡ እና ፡ ከጭቃ
  እሳት ፡ ሲያገኘው ፡ ሆነ ፡ የክብር ፡ ዕቃ
  ጠንክሬ ፡ በርትቼ ፡ እንድመላለስ
  ልቤን ፡ አጀገነው ፡ ቅዱሱ ፡ መንፈስ
  ቀዝቃዛ ፡ ሂወቴ ፡ በፈተናው ፡ ሞቀ
  እሳቱ ፡ ሲነካው ፡ ነጠረ ፡ ደመቀ
  ዘመኔ ፡ እንዲደምቅ ፡ እንዲያበራ
  መቼ ፡ መሰለኝ ፡ የምሰራ
  ልክ ፡ እንደ ፡ ድንጋይ ፡ ተራ ፡ የነበረ
  እሳት ፡ ሲያገኘው ፡ ሆነ ፡ የከበረ
  ለመልካም ፡ ሆነልኝ ፡ ሆነልኝ (2X)
  ለበጎ ፡ ሆነልኝ ፡ ሆነልኝ (2X)
  ለመልካም ፡ ሆነልኝ ፡ ሆነልኝ
  ለመልካም ፡ ሆነልኝ ፡ ያስጨነከኝ
  ለበጎ ፡ ሆነልኝ ፡ ሆነልኝ
  ለበጎ ፡ ሆነልኝ ፡ ያስጨነከኝ
በመከራ ፡ ውስጥ ፡ መታዘዝን ፡ ተማረ
በስጋው ፡ ወራት ፡ አንተን ፡ አከበረ
እኛ ፡ ዳንን ፡ እንጂ ፡ በእርሱ ፡ መከራ
ህይወታችን ፡ ጣፍጧል ፡ በጠጣው ፡ መራራ
እሱ ፡ ኃያል ፡ ሳለ ፡ ምስኪን ፡ መሰለ
ከአመፀኞች ፡ ጋር ፡ ተሰቀለ
በጌታ ፡ መከራ ፡ ስንቶች ፡ ዳኑ
አቀረባቸው ፡ ወደ ፡ ዙፋኑ
  ጌታ ፡ ሆይ...