ሳይከፈል ፡ ባህሩ (Sayikefel Bahiru) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ገና ፡ ሳይከፈል ፡ ባህሩ
ሳይሳካ ፡ ነገሩ (፪x)
እስቲ ፡ ላንሳ ፡ ከበሮውን
ላመስግነው ፡ እግዚአብሔርን (፪x)

አመሰግናለሁ (፰x)

ዝም ፡ አልልም ፡ አመሰግናለሁ
ለጌታዬ ፡ ክብርን ፡ እሰጣለሁ
የጠላቴን ፡ ንዝነዛ ፡ እምቢ ፡ ብዬ
ላመስግነው ፡ ላክብረው ፡ ጌታዬ

አመሰግናለሁ (፰x)

ሁኔታ ፡ መጣና ፡ ጠየቀኝ
ዛሬም ፡ ታመልኪያለሽ ፡ ወይ ፡ አለኝ
ነገሮች ፡ መጡና ፡ ጠየቁኝ
ዛሬም ፡ ታመልኪያለሽ ፡ ወይ ፡ አሉኝ

አዎ ፡ አመልካለው ፡ እባርከዋለሁ
አዎ ፡ አመልካለው ፡ ከፍ ፡ አደርገዋለሁ (፪x)

ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጎ ፡ እንዲደረግ
ክፉ ፡ ሁሉ ፡ ለጥሩ ፡ እንዲለወጥ
ይህንንም ፡ ጨምሬ ፡ አውቃለሁ
ስለዚህም ፡ አመሰግናለሁ

አመሰግናለሁ (፰x)

ሁኔታ ፡ መጣና ፡ ጠየቀኝ
ዛሬም ፡ ታመልኪያለሽ ፡ ወይ ፡ አለኝ
ነገሮች ፡ መጡና ፡ ጠየቁኝ
ዛሬም ፡ ታመልኪያለሽ ፡ ወይ ፡ አሉኝ

አዎ ፡ አመልካለው ፡ እባርከዋለሁ
አዎ ፡ አመልካለው ፡ ከፍ ፡ አደርገዋለሁ (፪x)