From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
ማንም ፡ ሊፈታው ፡ አይችልም
ነገሬን ፡ ጉዳዬን ፡ ጌታ ፡ ሆይ (፪x)
አንተ ፡ ጋር ፡ መጣለው
ይዜው ፡ ነገሬን ፡ ጉዳዬን (፪x)
ፈቺ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ፈቺ ፡ ነህ
ፈቺ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ፈቺ ፡ ነህ
ፍቅሩ ፡ ተፈትኖ ፡ ወርቅ ፡ ሆኖ ፡ ተገኝቶአል
በመከራ ፡ አልፎ ፡ ነፍሱን ፡ ለእኔ ፡ ሰጥቶአል
እራሱን ፡ አዋርዶ ፡ ፍቅሩን ፡ አሳይቷል
ከፍቅሮችም ፡ በላይ ፡ የእርሱ ፡ ፍቅር ፡ በልጧል
ማንም ፡ የለኝ ፡ ከኢየሱስ ፡ በላይ
ስመላለስ ፡ በዚች ፡ ምድር ፡ ላይ
ነፍሱን ፡ ለእኔ ፡ ቤዛ ፡ ያደረገው
እውነተኛ ፡ ወዳጄ ፡ እርሱ ፡ ነው
ለህይወቴ ፡ ፍቺ ፡ ትርጉምን ፡ የሰጠው
ኑሮዬን ፡ አጣፍጦ ፡ እንዲህ ፡ ያደረገው
በእውነተኛ ፡ ፍቅሩ ፡ ያዳነኝ ፡ የመራኝ
ከኢየሱስ ፡ የሚበልጥ ፡ ለእኔ ፡ ማንም ፡ የለኝ
ማንም ፡ የለኝ ፡ ከኢየሱስ ፡ በላይ
ስመላለስ ፡ በዚች ፡ ምድር ፡ ላይ
ነፍሱን ፡ ለእኔ ፡ ቤዛ ፡ ያደረገው
እውነተኛ ፡ ወዳጄ ፡ እርሱ ፡ ነው
ለክፉዎችም ፡ ቸር ፡ የሀጢያተኛ ፡ ወዳጅ
ከጥፋት ፡ ሚመልስ ፡ ለሰዎች ፡ የሚበጅ
ልብን ፡ የሚነካ ፡ ንግግሩ vጣፋጭ
እውነተኛ ፡ መሲሕ ፡ ቅዱስ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ
ማንም ፡ የለኝ ፡ ከኢየሱስ ፡ በላይ
ስመላለስ ፡ በዚች ፡ ምድር ፡ ላይ
ነፍሱን ፡ ለእኔ ፡ ቤዛ ፡ ያደረገው
እውነተኛ ፡ ወዳጄ ፡ እርሱ ፡ ነው
እኔ ፡ መኖር ፡ አልችል ፡ ስምህን ፡ ሳልጠራ
አንተ ፡ በህይወቴ ፡ አለህ ፡ ትልቅ ፡ ስፍራ (፪x)
እኔ ፡ መዋል ፡ አልችል ፡ ስምህን ፡ ሳልጠራ
አንተ ፡ በህይወቴ ፡ አለህ ፡ ትልቅ ፡ ስፍራ (፪x)
እኔ ፡ ማደር ፡ አልችል ፡ ስምህን ፡ ሳልጠራ
አንተ ፡ በህይወቴ ፡ አለህ ፡ ትልቅ ፡ ስፍራ (፪x)
እኔ ፡ መዋል ፡ አልችል ፡ ስምህን ፡ ሳልጠራ
አንተ ፡ በህይወቴ ፡ አለህ ፡ ትልቅ ፡ ስፍራ (፪x)
ያለምንም ፡ መኖር ፡ እችላለው
ደግሞም ፡ አይደልቀኝም ፡ ኖሬ ፡ አይቼዋለው
ግን ፡ ያላንተ ፡ ጌታ ፡ እንዴት ፡ እኖራለው
ግን ፡ ያላንተ ፡ ኢየሱስ ፡ እንዴት ፡ እኖራለው
|