የልቤ አምላክ (Yelibe Amlak) - አስቴር ፡ አበበ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዋላ ወደ ውሃ ምንጭ እንደምትናፍቅ
         ነፍሴ ወደ አንተ ትገሰግሳለች
ዋላ ወደውሃ ምንጭ እንደምትናፍቅ
ነፍሴ ወደ አንተ ትገሰግሳለች

ቅርቤ ሆነህ ግን ነክቼ ያልጨረስኩህ
የምትገባኝ ግን አውርቼ ያልቋጨሁህ
የጨበጥኩህ ግን እሮጬ ያልደረስኩብህ
የማወራህ ግን በቂ ቃል ያጣሁልህ

እየበላሁህ የምትርበኝ
እየጠጣሁህ የምትጠማኝ
እየበላሁህ የምትርበኝ
እየረካሁህ የምትጠማኝ

ሁሌ እያየሁህ የምትናፍቀኝ
ሁል ጊዜ አንተ ነህ የምታሰኘኝ
አብሬህ እየዋልኩ የምትናፍቀኝ
ሁል ጊዜ አንተ ነህ የምታሰኘኝ

የተማርኩህ ግን እንዲህ ነህ የማልልህ
ያስደነቅኸኝ ግን በቂ ቃል ያጣሁልህ
የማብራራህ የቃል አቅም የሚያጥረኝ
ያንተ ፍቅር እንዲህ ነው የሚያደርገኝ

የልቤ አምላክ የምከተልህ
እስካይህ ድረስ የምናፍቅህ
የልቤ አምላክ የምከተልህ
እስካይህ ድረስ የምናፍቅህ
የበረሃ ጥሜን ያረካሁብህ
አንተ የህይወት ውሃዬ ነህ
የበረሃ ጥሜን ያረካሁብህ
አንተ የህይወት ውሃዬ ነህ

የምወድህ ውዴ የማፈቅርህ ፍቅሬ
የምከተልህ እረኛዬ ምሰግድልህ አምላኬ
አንተን ከአገኘሁ ሁሉን እረሳለሁ
አንተን ከአገኘሁ ረክቼ አድራለሁ
አንተን ከአገኘሁ ሁሉን እረሳለሁ
አንተን ከአገኘሁ ረክቼ አድራለሁ