From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
በአመፅ ተፀንሶ ኃጢአት ሆና እናቱ ሞት ለሆነ አለሙ
ሲኦል መደምደሚያው እንዲሆን ለታጨ ታይቶህ መባዘኑ
ሩቅ ለነበረ ህዝብ ወደ ግዛትህ መጥሪያ አቁመህ ምልክት
ከምድር ዳርቻ ጠራህ በፉጨትህ ያላወቀህን ትውልድ
እየተጣደፍን በፍጥነት መጥተናል
ድካም ድንዛዜን ፍርሃት ጨለማን ከኛ ላይ ሰብረሃል
የተናቅነውን ምርጥ የተጣልነውን ቅዱስ ልትለን ያላፈርህ
የጸጋ ሁሉ አምላክ የሆንህ እግዚአብሄር ክቡር ስምህ ይባረክ
ምህረት ለወደደ ለሮጠም አይደለ
መማርን በምታውቅ በአንተ ለኛ ሆነ
ለፍቅርህ ማሳያ ህዝብ ብለህ መረጥከን
ለጥፋት ለሆንን የቁጣ እቃዎች ትዕግስትህ ቻለን
የህግ መሰጠት የመቅደስ ስርዓት
ኪዳን ላልነበረን ውብ የተስፋ ቃላት
የጥሉ ግድግዳ ከማዶ ላረገን
ዕውር ለስርአትህ አህዛብ ለተባልን
ላክልን ለነፍሳችን መልህቅ
ሊቀ ካህን ከሙሴ የሚልቅ
ላክልን ለነፍሳችን መልህቅ
ሊቀ ካህን ከአሮን የሚልቅ
የህልውናህን ስፍራ እንዳያይ አይናችን
ሆኖን መጋረጃ ከልሎ ሃጥያታችን
ይዞን እንዲገባ ከማዶ እንዳንቀር
ስለ እኛ ቀደመ ገባ በመካከል
ተልኮልን ለነፍሳችን መልህቅ
ሊቀ ካህን ከአሮን የሚልቅ
ላክልን ለነፍሳችን መልህቅ
ሊቀ ካህን ከሙሴ የሚልቅ
የእንቅፋት ድንጋይ ማሰናከያ አለት
አኑሮ በጽዮን አምነው እንዲድኑበት
በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን
ቅን ፈቃዱ ሆና ጥንት ተወስኖልን
ተልኮልን ለነፍሳችን መልህቅ
ሊቀ ካህን ከሙሴ የሚልቅ
ላክልን ለነፍሳችን መልህቅ
ሊቀ ካህን ከአሮን የሚልቅ
ተልኮልን ለነፍሳችን መልህቅ
ሊቀ ካህን ከአሮን የሚልቅ
ላክልን ለነፍሳችን መልህቅ
ሊቀ ካህን ከሙሴ የሚልቅ
|