ሃሌሉያ (Hallelujah) - አስቴር ፡ አበበ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
አስቴር ፡ አበበ
(Aster Abebe)

፪
(2)

ሃሌሉያ
(Hallelujah)

ዓ.ም. (Year): ፳፪፬"፳፪፬" is not in the list (፲ ፱ ፻ ፹ ፩, ፲ ፱ ፻ ፹ ፪, ፲ ፱ ፻ ፹ ፫, ፲ ፱ ፻ ፹ ፬, ፲ ፱ ፻ ፹ ፭, ፲ ፱ ፻ ፹ ፮, ፲ ፱ ፻ ፹ ፯, ፲ ፱ ፻ ፹ ፰, ፲ ፱ ፻ ፹ ፱, ፲ ፱ ፻ ፺ ፩, ...) of allowed values for the "ዓመተምህረት" property. (2024)
ቁጥር (Track):

፫ (3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ አበበ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Abebe)

በሰላሙ ፡ ብዛት ፡ ቀለለ ፡ ችግሩ
አደገ ፡ ቁመቴ ፡ እያለ ፡ ነገሩ
ቀረ ፡ መዋከቤ ፡ በጠራኸኝ ፡ ሳርፍ
ተምራልኝ ፡ ነፍሴ ፡ አንተ ፡ ላይ ፡ ማራገፍ

ድምጿ ፡ ተቀየረ ፡ ተለወጠ ፡ ቃ
 እዬዬን በእሰየው የአንተ በመሆኗ
እህህን በእልልታ ለምኑን በአሜን
ለለወጥከው እየሱስ እንካ ዘላለሜን
እዬዬን ፡ በእሰየው ፡ የአንተ ፡ በመሆኗ
እህህን ፡ በእልልታ ፡ ለምኑን ፡ በአሜን
ለቀየርከው ፡ እየሱስ ፡ እንካ ፡ ዘላለሜን

ተባረክ ፡ እልሃለሁኝ (፰x)

ተንበርክኬ ፡ አሸነፍኩኝ
እጅ ፡ ሰጥቼ ፡ ድል ፡ ነሳሁኝ
በጩኸቴ ፡ መዳን ፡ ሆነ
አበሳዬ ፡ ተከደነ
ተከትዬህ ፡ ከፊት ፡ ቀደምኩ
ያንተን ፡ ብዬ ፡ ከምን ፡ ጎደልኩ
ስፈልግህ ፡ ጸኑ ፡ እግሮቼ ፡ ሃይሌ ፡ ሆነኸኝ ፡ ተሟጋቼ

በመጨነቅ ፡ ስርአትህን
በመማጸን ፡ መጓደድን
በር ፡ በመዝጋት ፡ ክፉን ፡ ማምለጥ
እርዳኝ ፡ ብዬ ፡ ሁሉን ፡ መብለጥ
ከአንተ ፡ ሰምቶ ፡ የውስጥ ፡ ውበት
አቤት ፡ ብዬህ ፡ አለኝ ፡ ማለት
ከአንተ ፡ ዘግኖ ፡ ሞልቶ ፡ ማደር
ሆኖልኛል ፡ ስምህ ፡ ይክበር

ስኬቴ ፡ በአንተ ፡ መታመኔ
ከፍታዬ ፡ እግርህ ፡ ስር ፡ መሆኔ
ውበቴ ፡ አንተን ፡ መጠጋቴ
ድምቀቴ ፡ ምህረትህ ፡ ነው ፡ ለኔ
ስኬቴ ፡ በአንተ ፡ መታመኔ
ከፍታዬ ፡ እግርህ ፡ ስር ፡ መሆኔ
ውበቴ ፡ አንተን ፡ መጠጋቴ
ድምቀቴ ፡ ምህረትህ ፡ ነው ፡ ለኔ

አሃ ሃሌሉያ/4 እላለሁ ሃሌሉያ

በማለዳ ሃሌሉያ በቀትር ሃሌሉያ
በምሽት ፡ ሃሌሉያ ፡ በሌሊት ፡ ሃሌሉያ
ሁሉ ፡ እንዳለ ፡ ሆኖ ፡ ሃሌሉያ
ሳይቀየር ፡ ሃሌሉያ
እላለሁ ፡ ሃሌሉያ

አሃ ፡ ሃ ፡ ሃ ፡ ሃሌሉያ (፪x)
ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ሃሌሉያ
አሃ ፡ ሃ ፡ ሃ ፡ ሃሌሉያ (፫x)
ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ሃሌሉያ
አሃ ፡ ሃ ፡ ሃ ፡ ሃሌሉያ
ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ሃሌሉያ