አንድ ቃል (And Kal) - አስቴር ፡ አበበ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ልንገርህ መውደዴን ለአንተ ያለኝን
ከሰፈር ከሰው አሸፍቶ ጥፍት የሚያደርገኝን
ልቤን ያጠፋውን ፋታ የማይሰጠኝን ሌላውን ለማሰብ
ምክንያት እየሆነ በር የሚያዘጋኝን በሰበባ ሰበብ

ፍቅር ነው የያዘኝ ፍቅር
እንደ መልህቅ ሆኖ ከሌላው ያስጣለኝ
ከአለም አጣልቶ ከአንተ ያጣበቀኝ ፍቅር

የምሬን ነው የምወድህ
ምርጫዬ አባቴ የኔ ፍቅር የምልህ
ምቾቴን የሚያተወኝ ያለኝን የሚያስንቀኝ
እጅ እጅህን ሳይሆን ፊትህን የሚያስናፍቀኝ ፍቅርህ ነው

ፍቅር ነው የያዘኝ ፍቅር
እንደ መልህቅ ሆኖ ከሌላው ያስጣለኝ
ከአለም አጣልቶ ከአንተ ያጣበቀኝ ፍቅር

ለውድድር የማይቀርብ የበረታ ፍቅር
በልጠህ የምትናፍቀኝ በተጠጋሁህ ቁጥር
ከፍዬ የማልሰጠው ለሌላው ቆርሼ
ልቤ እኮ የአንተ ነው የፍቅር ምላሼ
ከፍዬ የማልሰጠው ለሌላው ቆርሼ
ልቤ እኮ የአንተ ነው የፍቅር ምላሼ

ምን ብል አያረካኝ ደርሶም አያጠግበኝ
ሁሉ የተራቆተ የሚያስንስህ ሆነብኝ
አንድ ቃል አገኘሁ የምደጋግመው
ልቤ ላይ ጠብ ያለ ነጋ ጠባ የምለው
እንካ ይኸው እገሰግስሃለሁ
አንድ ቃል አገኘሁ የምደጋግመው
ልቤ ላይ ጠብ ያለ ነጋ ጠባ የምለው
እድሜ ልኬን እኔ እፈልግሃለሁ