እግዚአብሔርን አየሁ (Egziabherin Ayehu) - አስቴር ፡ አበበ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ለሁሉ ነፍስ ዘሪ ነህ
ፍጥረት ያላንተ ባዶ ነው
በአፍህ ቃል ጸንቶ ቆሟል ሁሉ
አንድ ብሎ ቢራመድ በአንተ ነው
ሁሉ ባዶ ጨለማ አንዳች በማይገኝበት
ከሌለው ይህን ሁሉ ሞልተሃል አቤት ችሎታህ ያስብላል
ሁሉ ባዶ ጨለማ አንዳች በማይገኝበት
ከሌለው ይህን ሁሉ ፈጥረሃል አቤት ችሎታህ ያስብላል

ቃላት የማይገልጽህ የማትብራራ
የማትሰፈር የማትሰላ
ልክህ ከቋንቋዎች ሰፈር የለ
አንተ እራስህ አንተነህ
ልክህ ከቁጥሮች መንደር የለ
አንተ እራስህ አንተ ነህ
ልክህ ከቋንቋዎች ሰፈር የለ
አንተ እራስህ አንተነህ
ልክህ ከቁጥሮች መንደር የለ
አንተ እራስህ አንተ ነህ

የሰማዩን ደመና በጥበብ ቆጥረሃል
መብረቅ ሊታዘዝህ እነሆኝ ይልሃል
የምድሩን ውሃ በእፍኝህ የቋጠርክ
የምስራቁን ንፋስ በምድር ላይ የበተንክ
ለማዕበሉ ትዕቢት ገደብ ይሁን ያልህ
ሁሉን አሰልፈህ ስርአት ያስያዝህ
በፍጥረትህ ታይተህ መደመም ሆነብኝ
በማይነጥፍ አንደበት ማመስገን ይብዛልኝ

በቃላት መደርደር በስንኝ ቋጠሮ
ማን አክትሞ ያውቃል ስላንተ ዘርዝሮ
ስራህ ለጠቢባን ሆናቸው መፍዘዣ
አጥንተው እንዳያርፉ የእድሜ ልክ መጓዣ
በጠብታ እውቀት ስንቱ አንጋጦ ቀረ
ላይጨርስ ጀምሮ ዝንት አለም ቆፈረ
ለኔ ግን በርቶልኝ የመስቀልህ እውነት
ስራዬ አደረኩት ፍቅርህን መቀኘት

አየሁ (4)
በፍጥረቱ እግዚአብሄርን አየሁ
አየሁ (4)
በእጁ ስራ እግዚአብሄርን አየሁ
አየሁ (4)
ሰማዩን ሳይ እግዚአብሄርን አየሁ
አየሁ (4)
እራሴን ሳይ እግዚአብሄርን አየሁ

ትልቅ ነው እግዚአብሔር ትልቅ ነው (2)
ተምሬአለሁ እግዚአብሔር ትልቅ ነው (2)
አይቻለሁ እግዚአብሔር ትልቅ ነው(2)
አውቄአለሁ እግዚአብሔር ትልቅ ነው(2)