አሜን (Amen) - አስቴር ፡ አበበ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
አስቴር ፡ አበበ
(Aster Abebe)

፪
(2)

አልበም
(Hallulejah)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፩ (1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስቴር ፡ አበበ ፡ አልበሞች
(Albums by Aster Abebe)

ውሉን አልሳተም የህይወቴ ድውር
ስትክሰኝ አየሁ ስታሰማምር
አንድ ብለህ እንደ ጀመርክ ብክብር ስለምትቋጨው
ዝም ብዬ ልዘምር ይሁን አንተ እንዳልከው
 
ያልከው ይሁን እሺ እሺ በቃ
ነፍስ ትረፍልኝ ያልክላትን አውቃ
 
በወደድኩት ሳይፈስ ለኔ በተመቸኝ
የህይወቴ ጎዳናው ለምን ሲያሰኘኝ
ሁሉን አያይዞ ለበጎ ሲያደርግ
በዓይኔ በብረቱ አየሁት ሲለውጥ
ርስቱን ሲያድል ነጥቆ ከዚያ ሰነፍ
ዘወትር ለሚተጋው ሊያልቀው ሲሰለፍ
ትናንት እንደሆነው ዛሬም እንደዚያው ነው
ስፍራን ላልለቀቀ በቦታው ለቆየው
 
አሜን አሜን
ያለው ይሁን እሺ እሺ በቃ
ነፍስ ትረፍልኝ ያለላትን አውቃ
 
የገዢ ቁጣ ሲነድ በላዬ
ፍንክች ላልል ላለቅ ስፍራዬን
በትዕግስት ስፋት መቆየት ላደርግ
ታላቁን ጥፋት ፀጥ እስክታደርግ
እንድኖር በቃልህ ልቤን አስፋልኝ
ቀን እስኪመጣ እስክትፈርድልኝ
ያደከመኝን እክታደክመው
የበቀል ጣትህን ዓይኔ እስኪያየው
ድቅድቁን ስታዝዝ ላይቀር መንጋቱ
ጎህ ሊቀድልኝ ሊያልፍ ሌሊቱ
የቀረ ይመስላል አንዲት እርምጃ
 
ተራራው ሊናድ ሊሆን መሄጃ የወጀቡ አዛዥ
የተራራው ሠሪ የሸለቆው ጌታ የጨለማው መሪ
የማዕበሉ አዝማች የመብረቁ ንጉስ
አንተ ነህ የኔ አባት የእስራኤል ቅዱስ
 
የወጅቡ አዛዥ የተራራው ሠሪ
የሸለቆው ጌታ የጨለማው መሪ
የማዕበሉ አዝማች የመብረቁ ንጉስ
አንተ ነህ የኔ አባት የእስራኤል ቅዱስ