እራስህ አስተማርከኝ (Erasih Asteamarikegn) - አስቴር ፡ አበበ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ስንፍና ላይ እንዳልከርም እንዳልቆይ በዝለት
ሁሉ ከአቅም በልጦ ከልክ ያለፈ ዕለት
ስንፍና ላይ እንዳልከርም እንዳልቆይ በዝለት
ሁሉ ከአቅም በልጦ ከልክ ያለፈ ዕለት
ሳላመልክህ እንዳልቀር ከልምዴ እንዳልጎድል
ሸክሜን ለአንተ አራግፌ መዘመር እንድቀጥል
ከጣራዬ በታች ያለው እንዳይዘኝ
ወጣ ብሎ ማምለክን እራስህ አስተማርከኝ
ከጣራዬ በታች ያለው እንዳይዘኝ
እልፍ ብሎ ማምለክን እራስህ አስተማርከኝ

ለአምላክነትህ ስግደቴ ይኸው
ጥያቄ የለኝም ፊትህ የማቀርበው
አይኔን የሚሰርቅ በልጦ ከፍቅርህ
ልቤን የሚያሸፍት ገኖ ካሳብህ
ጉዳይ የለኝም ከአንተ የሚያጎድለኝ
ቁም ነገሬ ነህ ሌላ ምን አለኝ
ጉዳይ የለኝም ከአንተ የሚያጎድለኝ
ቁም ነገሬ ነህ ሌላ ምን አለኝ

ለአምላክነትህ ስግደቴ ይኸው
ጥያቄ የለኝም ፊትህ የማቀርበው
አይኔን የሚሰርቅ በልጦ ከፍቅርህ
ልቤን የሚያሸፍት ገኖ ከሃሳብህ
ጉዳይ የለኝም ከአንተ የሚያጎድለኝ
ቁም ነገሬ ነህ ሌላ ምን አለኝ
ጉዳይ የለኝም ከአንተ የሚያጎድለኝ
ቁም ነገሬ ነህ ሌላ ምን አለኝ

አገኘሁህ ከሚነደው እሳት መሃል
እንዳልችለው አውቀህ ፈጥነህ ተገኝተሃል
የፍርሃቱን ሽታ የእሳቱን ግለት
ቀድመህ በህልውናህ ስታሳጣው ጉልበት
ቀርቶ የሞት ዜና ሲወራ መኖሬ
ኧረ እንዴት አልጨምር በላይ በላይ ቅኔ
ቀርቶ የሞቴ ዜና ሲወራ መኖሬ
ኧረ እንዴት አልጨምር በላይ በላይ ቅኔ

አገኘሁህ ከሚነደው እሳት መሃል
እንዳልችለው አውቀህ ፈጥነህ ተገኝተሃል
የፍርሃቱን ሽታ የእሳቱን ግለት
ቀድመህ በህልውናህ ስታሳጣው ጉልበት
ቀርቶ የሞት ዜና ሲወራ መኖሬ
ኧረ እንዴት አልጨምር በላይ በላይ ቅኔ
ቀርቶ የሞቴ ዜና ሲወራ መኖሬ
ኧረ እንዴት አልጨምር በላይ በላይ ቅኔ

ለአምላክነትህ ስግደቴ ይኸው
ጥያቄ የለኝም ፊትህ የማቀርበው
አይኔን የሚሰርቅ በልጦ ከፍቅርህ
ልቤን የሚያሸፍት ገኖ ከሃሳብህ
ጉዳይ የለኝም ከአንተ የሚያጎድለኝ
ቁም ነገሬ ነህ ሌላ ምን አለኝ
ጉዳይ የለኝም ከአንተ የሚያጎድለኝ
ቁም ነገሬ ነህ ሌላ ምን አለኝ

ለአምላክነትህ ስግደቴ ይኸው
ጥያቄ የለኝም ፊትህ የማቀርበው
አይኔን የሚሰርቅ በልጦ ከፍቅርህ
ልቤን የሚያሸፍት ገኖ ከሃሳብህ
ጉዳይ የለኝም ከአንተ የሚያጎድለኝ
ቁም ነገሬ ነህ ሌላ ምን አለኝ
ጉዳይ የለኝም ከአንተ የሚያጎድለኝ
ቁም ነገሬ ነህ ሌላ ምን አለኝ