ነፍሴን በፊትህ (Nefsen Befiteh) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ነፍሴን በፊትህ አፈሣለው ይኸው 2×
ጌታ ምሥጋናዬን ዝም አትበለው
ተቀበለው ይኸው 2×

ስምህ በእኔ ላይ ተጠርቷልና
የመጥራቱ ተስፋ ገብቶኛልና
ልሣኔ ባንተ ሃሴት አረገ
ልቤም ሁል ጊዜ አንተን ፈለገ

ነፍሴን በፊትህ አፈሣለው ይኸው 2×
ጌታ ምሥጋናዬን ዝም አትበለው
ተቀበለው ይኸው

ያከበሩህን ታከብራለህ
የሚወዱህን ትወዳለህ
ተግተው ለሚሹህ ትገኛለህ
እግዚአብሔር አምላክ እንደቃልህ

እራሴን ከእግርህ በታች አዋርዳለው /3×
በጊዜው ከፍ የሚያደርግ እንዳንተ ማነው /3×

ያከበሩህን ታከብራለህ
የሚወዱህን ትወዳለህ
ተግተው ለሚሹህ ትገኛለህ
እግዚአብሔር አምላክ እንደቃልህ