Kalkidan Tilahun/Chelemayen Geta Eyabera/Betalaq Girma Bezufanu Lalew
Jump to navigation
Jump to search
ዘማሪ ፡ ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን
ርዕስ ፡ በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በዙፋኑ ፡ ላለው
ጨለማየን ፡ ጌታ ፡ እያበራ
በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በዙፋኑ ፡ ላለው
የምስጋና ፡ ዘውድ ፡ በራሱ ፡ ለጫነው
እዘምራለሁ (4x)
እኔ ፡ አፌን ፡ አልከፍትም ፡ ለአለም ፡ ክብር
እዘምራለሁኝ ፡ ለእግዚአብሔር (2)
እቀኝለታለሁ ፡ በአዲስ ፡ አዲስ ፡ ዜማ
የምስጋናየ ፡ ድምፅ ፡ በአርያም ፡ ይሰማ (2x)
በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በዙፋኑ ፡ ላለው
የምስጋና ፡ ዘውድ ፡ በራሱ ፡ ለጫነው
እዘምራለሁ (4x)
በጠዋት ፡ በማታ ፡ በቀን ፡ በሌሊቱ
እሰዋለታለሁ ፡ ምስጋናን ፡ በፊቱ (2x)
እያደነኩና ፡ እየተደነኩ
እግዚአብሔር ፡ አምላኬን ፡ አመልከዋለሁ (2x)
በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በዙፋኑ ፡ ላለው
የምስጋና ፡ ዘውድ ፡ በራሱ ፡ ለጫነው
እዘምራለሁ (4x)
በታላቅ ፡ ጉባኤ ፡ ሰውም ፡ በበዛበት
ለእስራኤል ፡ ቅዱስ ፡ ቅኔን ፡ ልቀኝለት (2x)
ከንፈሮቼም ፡ እጅግ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ አላቸው
ዝማሬ ፡ ሲያቀርቡ ፡ ለፈጣሪያቸው (2x)
በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በዙፋኑ ፡ ላለው
የምስጋና ፡ ዘውድ ፡ በራሱ ፡ ለጫነው
እዘምራለሁ (4x)