Kalkidan Tilahun/Chelemayen Geta Eyabera/Chelemayen Geta Eyabera
Jump to navigation
Jump to search
ዘማሪ ፡ ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን
ሌላ ፡ ሥም ፡ ሊሊ
ርዕስ ፡ ጨለማዬን ፡ ጌታ ፡ እያበራ
አልበም ፡ ጨለማዬን ፡ ጌታ ፡ እያበራ
ጨለማዬን ፡ ጌታ ፡ እያበራ
በእሳት ፡ በደመና ፡ እየመራ
ክፉ ፡ በሆኑብኝ ፡ ቀኖች ፡ ፈንታ
ደስታን ፡ አጠገበኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ
ምን ፡ እላለሁ ፡ ምስጋናን ፡ ተሞልቻለሁ
ምን ፡ እላለሁ ፡ ጌታ ፡ አምላኬን ፡ አከብራለሁ
አንተ ፡ ለኔ ፡ ያደረከው
ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
በጎነትህ /ቸርነትህ/ አያልቅም
ባወራው ፡ ብዘምረው
የፊቱ ፡ ብርሃን ፡ አበራልኝ
በልቤም ፡ ደስታን ፡ ጨመረልኝ
ጌታ ፡ ምህረቱ ፡ እረድቶኛል
ሃዘኔን ፡ ችግሬን ፡ አስትቶኛል (2x)
ምን ፡ እላለሁ ፡ ምስጋናን ፡ ተሞልቻለሁ
ምን ፡ እላለሁ ፡ ጌታ ፡ አምላኬን ፡ አከብራለሁ
አንተ ፡ ለኔ ፡ ያደረከው
ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
በጎነትህ/ቸርነትህ ፡ አያልቅም
ባወራው ፡ ብዘምረው
ለልቤ ፡ እንደመከራዋ ፡ ብዛት
ማፅናናትህ ፡ ነፍሴን ፡ ደስ ፡ አሰኛት
እግዚአብሔር ፡ ከላይ ፡ አስቦኛል
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ደስ ፡ ይለኛል (2x)
ምን ፡ እላለሁ ፡ ምስጋናን ፡ ተሞልቻለሁ
ምን ፡ እላለሁ ፡ ጌታ ፡ አምላኬን ፡ አከብራለሁ
አንተ ፡ ለኔ ፡ ያደረከው
ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
በጎነትህ/ቸርነትህ/ደግነትህ/ፍቅርህም ፡ አያልቅም
ባወራው ፡ ብዘምረው