ይኑርልን ፡ ጌታ (Yinurelen Gieta) - በረከት ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
በረከት ፡ ለማ
(Bereket Lemma)

፩
(1)

አልበም
(1)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፯ (7)

ርዝመት (Len.): 5:47
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Lemma)

ያደርንበት ኃጢአት ከንስሃ ጣፍጦ

እግዚአብሔርን መፍራት ተንቋል አመፅ በዝቶ

አንዳችን በኃጢአት ከሌላው ለመላቅ

ተፎካከርን ጌታን ከቤቱ ለማራቅ

 

አይታገልም ጌታ ከአፍኒና

ከፊንሃስ ጋራ

ይርቃል እንጂ ከማይፈሩት

ትራፊ እየሰጡ ከሚንቁት

ኢካቦድ ሆኖ በሐገሪቱ

በእልልታ ቢቀለጥ መንደሩ

አደንድኗል አመፅ ልባቸውን

እስኪሰጥ በጅራፍ ዋጋቸውን

 

ና.. ባደባባይ ስምህ ተሰድቧል

ና. ና መልሰን ፊትህ ወድቀናል

ና.... የተወሰደው ክብር ይመለስ

ና. ና አንተ ቆይልን ሚሄድ ይሂድ

 

ሙሽራው እያለ ሎሌው ደምቆ

ነውር የማይፈራ ምህረቱን ተለማምዶ

ሙሽሪትም ደጇን ለሌላው ከፍታ

በአላፊው አግዳሚው ጨረሰች ዘይቷን

 

የለበትም ጌታ በምስባኩ

በተዘጋዘጀው በስሙ

ይሰበካል እንጂ የሰው ዝና

ባሪው ከጌታው ልቋልና

አይጠራም ኢየሱስ በመድረኩ

አይነገርም ከቶ ትምህርቱ

ይሰበካል እንጂ ታምራቱ

ለንግድ የሚሆን ጥራዝ ጥቅሱ

 

ይኑርልን ጌታ በቤቱ

ይሰንብት ለርስቱ

ሚፈልገው አለ ከነፍሱ

የማይኖር ያለ እሱ

ባይተዋር አናርገው አንግፋው ይኑርልን ጌታ

ዝም ማለቱን አንናቅ ምህረቱ ሲበዛ

 

ላይ ላያችን ሲታይ ጣዖት ተፀያፊ

በቤተ መቅደስ ግን ከእግዜር እጅ ዘራፊ

በድፍረት ልምምድ ጌታን ስንጋፋ

የምህረት ደጁን እግዜር እንዳይዘጋ

 

ና.. ባደባባይ ስምህ ተሰድቧል

ና. ና መልሰን ፊትህ ወድቀናል

ና.... የተወሰደው ክብር ይመለስ

ና. ና አንተ ቆይልን ሚሄድዉ ይሂድ