አንተን ፡ ባየ ፡ ዓይኔ (Anten Baye Aynie) - በረከት ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
በረከት ፡ ለማ
(Bereket Lemma)

፩
(1)

አልበም
(1)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፫ (3)

ርዝመት (Len.): 5:33
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Lemma)

ሳይነጋ ሌሊቱ ሳትቀድመኝ ጀምበር

መጥቻለሁ ፊትህ ሌሊት ላልከኝ ጉዳይ

አንተን ባየ አይኔ ይስሀቄን አይቼ ንቄዋለሁ /የኔን ሳቅ

ሳላንገራግር ሳራን ሳላማክር እሰዋዋለሁ /ሰዎች ሳላማክር

 

ይሁና የኔ ሳቅ ለሱ ይሁና ደስታዬ ለሱ

ይበሉኝ ባዶ የቀረ ይበሉኝ የተሞኘ *2

 

ቀሎብኝ አይደለም ረብ ሚሆነኝ ለኔ

ጠብቄ ያገኘሁት ሚሳሳለት አይኔ

እርሱን አየሁና ትምክህቴ በሙሉ ንቄዋለሁ

ድጋሚ ሳላስብ ግራ ቀኝ ሳላይ ሰጠዋለው

 

ሞኝ ነህ ይበሉኝ

ያለህን ይበሉኝ

መካሪ አጣህ ይበሉኝ

ተሳሳትክ ይበሉኝ

እርሱን ካከበረ ከተቀበለልኝ ምን እሻለሁ

ካለኝ ብቻ ሳይሆን ራሴንም ጨምሬ ሰጠዋለሁ

 

ይሁና የኔ ሳቅ ለሱ ይሁና ደስታዬ ለሱ

ይበሉኝ ባዶ የቀረ ይበሉኝ የተሞኘ

ካረካህ አንተን ደስ ካሰኘህ

ሰዊልኝ ያልከው ደስታዬን ቢሆን / ታሪኬን

አንድ ሌሊት አይደር አንድ ቀን አይዋል

ሰዊልኝ ያልከው በኔ ቤት አያድር