ፀጋ ፡ ጨመረልኝ (Tsega Chemerelgn) - በረከት ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
በረከት ፡ ለማ
(Bereket Lemma)

፩
(1)

አልበም
(1)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Lemma)

ጸጋ ጨመረልኝ ምህረቱን አበዛልኝ
በፈተናዬ መሀል ፍቅሩን አየሁኝ
ጸጋ ጨመረልኝ ምህረቱን አበዛልኝ
በችግሬ መሃል ትዕግስቱን አየሁኝ
አየሁኝ አሻቅቤ አየሁት ይሄንን ጌታ
አየሁኝ ኢየሱስን ከእልፍ ጥያቄ መሃል


ደስ ይለኛል እታመናለሁ ልቤም አይፈራ
ደስ ይለኛል ስሙ አጥሬ ቅጥሬ ሆኖኛል

 
እንዳመጣጡ እንደ ላባ ልብ ቢሆን
ባትታደገኝ አትንካው ባዬ ባትሆን
አቅም አልነበረኝም ለመሸሽ ሚሆን ብርታት
ደርሰህ ባታስጥለኝ ባታድናት ይህችን ነፊሴን

ደስ ይለኛል እታመናለሁ ልቤም አይፈራ
ደስ ይለኛል ስሙ አጥሬ ቅጥሬ ሆኖኛል

ባለፉት ቀናቶች ለልቤ ተስፋ ሳጣ
ነፍሴ ተጨንቃ በተከበበ ከተማ
አይኖቼ ቀና አድርጌ አየውህና ረካው
መከራዬ መሀል ጥበቃህን ተረዳው

ደስ ይለኛል እታመናለሁ ልቤም አይፈራ
ደስ ይለኛል ስሙ አጥሬ ቅጥሬ ሆኖኛል

ጸጋ ጨመረልኝ ምህረቱን አበዛልኝ
በፈተናዬ መሀል ፍቅሩን አየሁኝ
ጸጋ ጨመረልኝ ምህረቱን አበዛልኝ
በችግሬ መሃል ትዕግስቱን አየሁኝ

አየሁኝ አሻቅቤ አየሁት ይሄንን ጌታ
አየሁኝ ኢየሱስን ከእልፍ ጥያቄ መሃል

ደስ ይለኛል እታመናለሁ ልቤም አይፈራ
ደስ ይለኛል ስሙ አጥሬ ቅጥሬ ሆኖኛል