ትሁን ፡ ፈቃድህ (Tihun Feqadeh) - በረከት ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
በረከት ፡ ለማ
(Bereket Lemma)

፩
(1)

አልበም
(1)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፩ (1)

ርዝመት (Len.): 5:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Lemma)

አንተ አሳብቤ ለጥቅሜ የፀለይኩት ፀሎቴ / አስታክኬ/

ፊትህን ሳይሆን እጅህን እያየሁ የወሰድኩት መልሴ
ህይወት ይሆናል ወይ ፊትህ ያልበራበት ምን ቢገኝ
ፀሎቴ ይገራ ልመናዬ ይመር መንፈስህ ያስተምረኝ

ትሁን ፈቃድህ በኔ አይሁን እኔ ያልኩት ለኔ
ትሁን ፈቃድህ በኔ አይሁን እኔ ያልኩት ለኔ

ስለ አባትነትህ ሳይሆን ስለ ክርክሬ ራርተህ
ደጅህን ስለጠናሁኝ እዬዬ ማለቴን አይተህ
ፀሎቴን እንዳትሰጠኝ ካልሆነ ያንተ ደስታ
እንደ ቃዬል ጠብቀኝ ብዬ ከፊትህ እንዳልወጣ

አንተ የሌለህበትን ፊትህ ያልበራበትን
አትስጣት ለነፍሴ ካንተ ሚለየኝን
አንተ ሳትኖር በኔ ብትሰጠኝ ከነዓኔን
በምን እለያለሁ ከሌላው ህዝብ እኔ

ትሁን ፈቃድህ በኔ አይሁን እኔ ያልኩት ለኔ
ትሁን ፈቃድህ በኔ አይሁን እኔ ያልኩት ለኔ

አትህዲ ሰተኸኝ ከቤቴ
ያውልህ ብለህ ፀሎቴን / ምኞቴን
አሳልፈህ ለኔ አትስጠኝ /ለፈቃዴ እኔን
ደስ ያለህን ብቻ አድርግልኝ

ትሁን ፈቃድህ በኔ አይሁን እኔ ያልኩት ለኔ
ትሁን ፈቃድህ በኔ አይሁን እኔ ያልኩት ለኔ