በመጀመሪያ (Bemejemeriya) - በረከት ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
በረከት ፡ ለማ
(Bereket Lemma)

፩
(1)

አልበም
(1)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:24
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Lemma)

በመጀመሪያ ቃል ነበር ሌላ አልነበረም ፍጥረት ሳይፈጠር
ነበረ ተብሎ እንጂ ጅማሬህን አውቆ ማን ይናገራል
ስላንተ ሚያወጋ ከአንተ ቀድሞ የኖረ
አልኖረም… የህይወት መገኛ የፍጥረት ምንጭ ነህ
አልኖረም… ህይወት ባንተ ይገኛል ለሰው ብርሃን ሆኖአል

ፍጥረታት በቃል ሳይፈጠሩም በፊት
ቃል እግዚአብሔር ነበር የሚኖር ዘላለም
ቃልም ስጋ ሆኖ በኛ ዘንድ ያደረው
ዓለማት ሳይኖሩ እርሱ ያው እሱ ነው

በመጀመሪያ ቃል ነበር ሌላ አልነበረም ፍጥረት ሳይፈጠር
ነበረ ተብሎ እንጂ ጅማሬህን አውቆ ማን ይናገራል
ስላንተ ሚያወጋ ከአንተ ቀድሞ የኖረ
አልኖረም… የህይወት መገኛ የፍጥረት ምንጭ ነህ
አልኖረም… ህይወት ባንተ ይገኛል ለሰው ብርሃን ሆኖአል
 

አትለካም ከቶ በሰዎች መለኪያ
እልፍ ቃላት በዝቶ አንተን አያብራራ
እርጅና ተጭኖህ ደግፉኝ አትልም
ከስም ሁሉ በላይ የሆነ ስም አለህ

ፍጥረት ይኖራል ባንተ..
አያኖርህ አንተን
ህይወት ይኖራል ባንተ
አያኖርህ አንተን

የሁሉ መገኛ አንተ
የሁሉ ጅምር አንተ
በጊዜ አትለካም አንተ
ዘመን አይሽርህም አንተን